ኢቅረዕ

2.00 $

በይዘታቸው ትንሽ የሆኑ ነገር ግን ብዙሃኑን ማህበረሰብ ቁርአንን ማንበብ ያስቻሉ ሁለት መጽሐፍት አሉ፡፡ እነዚህም ‹‹ቃዒደቱል ባግዳዲያ›› እና ‹‹ቃዒደቱል ኑራኒያ›› ይባላሉ፡፡የመጀመሪያው ከዐረብኛ ፊደላት ጀምሮ እስከ ‹‹ዓምመ›› ምእራፍ የያዘ ሲሆን ለበርካታ ዓመታት በሀገራችን ብዙዎች ይህን መጽሐፍ ተጠቅመው ቁርአንን በመማር ለማንበብ በቅተዋል፡፡ ሁለተኛው ድግሞ በዐረብኛ አነባብ ላይ ብቻ ትኩረቱን በማድረግ ሰዎች በቀላሉ ቁርአንን እንዲያነቡ ለማስቻል የቀረበ ስራ ነው፡፡ በውስጡ ምንም አይነት የቁርአን ምእራፍ ያልያዘ ትኩረቱ ዐረብኛ እንዲነበብ ብቻ ያደረገ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ስራዎች ዐረብኛን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የዐረብኛ ህግጋትንም የሚያስተምሩ ስራዎች ናቸው፡፡ይህ ‹‹ኢቅረዕ›› የተሰኘው መጽሐፍ ለአማርኛ አንባቢዎች በቀላሉ ዐረብኛን ማንበብ እንዲችሉ ሁለቱንም ስራዎች በመጠቀም የተለያዩ ምሳሌዎችንና ማብራሪያዎችን ያካተተ ቁርአንን ለመማር ለሚሹ ሰዎች ቀሎ የቀረበ መጽሐፍ ነው፡፡

የመጽሐፍ ርዕስ፡ ኢቅረዕ
ዝግጅት፡ ሙከሚል ከማል
የገጽ ብዛት፡ 160

Category: