Weight | 193 g |
---|
Miscellaneous
ኢስላም ወርቃማው የሳይንስ ማዕከል
5.00 $
መጽሐፉ በዋናነት ኢስላም ወርቃማው የሳይንስ እና የሥልጣኔ ማዕከል መሆኑን ይዳስሳል፡፡ በተለይ ከ8ኛው እስከ 14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፡፡ ዓለም ጨለማ በነበረችበት ወቅት ኢስላም በሳይንሱ ዘርፍ በተለይም በዋናነት በአውሮፓ በርካታ ፈርቀዳጅ ግኝቶችን ለዓለም አበርክቷል፡፡ ከጊዜ በኋላ ሌሎቹ ሳይንቲስቶች የሙስሊሞቹን ግኝት የራሣቸው አደረጉት፡፡ መጽሐፉ ይህንና መሰል ጉዳዮችን ይዳስሳል፡፡
ዝግጅት ፡ ሙሐመድ ዐሊ
የገጽ ብዛት ፡
የታተመበት ዓመት ፡
ከመጽሐፉ ፡-
1. ኻሊድ ኢብን ዘይድ ይባላል፡፡ እ.ኤ.አ በ701 (በኛ በግምት 693/694 ዓ.ል) እንደሞተ ይነገራል፡፡ የትውልድ ቀኑ በውል አይታወቅም፡፡ በኬሚስትሪ ዘርፍ የተመራመረ ሙስሊም ሳይንቲስት ነው…
2. አውሮፓውያን ‘ገበር’ ይሉታል…፤ ምናልባት የልብስ የውስጥ ሽፋን ለማለት ይሆን? ምክኒያቱም ለታላቁ አንቶኒ ላቮይዘር መሰረት በመጣሉ አደባባይ የማናወጣህ የውስጥ ሊቃችን ለማለት ፈልገው ይሆናል፡፡ ነገሩ ከትርጉምም ችግር የመጣ ሊሆን ይችላል፡፡ የግብፁ መሪ ጀማል አብዱልናስር… ‘ገማል’ መባሉ ይታወቃል፡፡ ግመል የሚለው ቃል በአረብኛ ጀመል ነው፡፡ በእንግሊዝኛ ሲወረስ ደግሞ ካሜል ተብሏል፡፡ ገበር ‘ጃቢር’ ለማለት ነው…
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት