Weight | 65 g |
---|
ኢስላምን ለመረዳት
$8.00
ኢስላም የብዙ ምሁራን ምርምር ሥራ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ከመነሻው ጀምሮ ዛሬም ድረስ በርካቶች ኢስላምን እየመረመሩ ነው፡፡ አጥኚዎች ሙስሊሞችም ሙስሊም ያልሆኑም ሆነዋል አንዳንዶቹ ለክፉ አስበውት ራሳቸው በኢስላም ውስጥ ሰምጠው ይቀራሉ አንዳንዶቹ አቅቷቸው በመሐል ያቆማሉ፡፡ ኢስላም ቀላልና ግልጽ ሃይማኖት ነው፡፡ ኢስላማዊ ሕግን ታሪክን አስተሳሰብን ፍልስፍናን በተመለከተ መጠናቱ ክፋት አይኖረውም፡፡ ጠላቶቹ ለመጥፎ አስበውት ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ መጽሐፉ እስልምናን ሊረዱት በሚገባ መልኩ የሚስረዳ ነው፡፡
አዘጋጅ ፡ ሸይኽ ፕ/ር ዩሱፍ አልቀርዳዊ
ትርጉም ፡ ሐሰን ታጁ
የገጽ ብዛት ፡ 360
የታተመበት ዓመት ፡ ግንቦት 2004
ከመጽሐፉ ፡የኢስላም የመጀመሪያው ዓላማ ጥሩ ግለሰብን መፍጠር ነው። ለአላህ ምድራዊ ወኪል፣ ከሁሉም ፍጡራን ለተላቀው፣ በጥሩ ቅርጽና ይዘት ለተፈጠረው፣ በሰማያትም በምድርም ውስጥ ያሉ ጸጋዎች ሁሉ ለተገሩለት የሰው ልጅ ተገቢ የሆነ ስብእና ያለው ግለሰብ። ሰብአዊ ማንነቱ የጎላና የተሟላ፣ እንስሳዊ ማንነቱ የከሰመ ግለሰብ። ይህ ግለሰብ ነው የጥሩ ቤተሰብ፣ የጥሩ ማኅበረሰብና የጥሩ ኡምማህ መሠረት የሚሆነው። የዚህ ግለሰብ አበይት ባሕሪያት ቀጥለው ተዘርዝረዋል። …
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት