ኢስላማዊ እሴቶች

$11.00

አዘጋጁ በኢስላማዊ መጽሐፍ ዝግጅት ታላላቅ ሥራዎቻቸው ከሚባለው አንዱ ነው ይህ መጽሐፍ፡፡ የኢስላማዊ ማኅበረሰብ ሥርዓታዊ መዋቅር ምን መምሰል እንዳለበት በአማረ አገላለጽ ቁልጭ አድርጐ የሚያሳይ ነው፡፡ የኢስላማዊ የሥነ-ሕግ ብይኖችን የማስረጃ ጥቅሶችን ከቁርኣንና ሐዲስ በማጣቀስ የሙስሊም ምሁራን የሃሳብ ልዩነቶችን በማስማማት ሙስሊሙን ማኅበረሰብ ለማነጽ ጥረት አድርገዋል፡፡ መጽሐፉ የኢስላም ግላዊና ማኅበራዊ እስቶችን በመዘርዝር ፋይዳቸዉንም አጉልቶ ለማሳየት ይሞክራል፡፡
አዘጋጅ ፡ ሸይኽ ሐሰን አዩብ
ትርጉም ፡ ኡስታዝ ሐሰን ታጁ
የገጽ ብዛት ፡536
የታተመበት ዓመት ፡ነሐሴ 2004
ከመጽሐፉ ፡ የኢስላማዊ እሴቶችን በጥልቀት መዳሰሱ ዓላማ የሙስሊምን ሕሊና ከነበረበት ሰመመን ለማንቃት፣ በራሱና በኢስላም ላይ መልካምን እንጅ መጥፎን አመለካከት እንዳያስቀምጥ፣ የስልጣኔ ደረጃ ላይ የደረሰ ሙስሊም ማኅበረሰብ እንዲኖር ለማድረግ ነው። በእርግጥ የሰው ልጅ ክቡር የሆነ ሕይወት ያለው፣ ለተሻለ ደረጃ የሚተጋ፣ በእውነተኛ ብርሃን የሚያንፀባርቅ፣ ክፋትን፣ ክህደትን፣ መጥፎነትን የማያውቅ፣ በንጹሕ ፍጡራን ላይ በተለይ እነዚህ ንጹሕ ፍጡራን ነፍሳት ቢሆኑም እንኳ ርኅራኄ ያለው፣ በራሱ (በነፍሱ) ኩሩ የሆነ፣ በእውነታ ላይ የማይተኛ፣ ለበደል እጅ የማይሰጥ፣ ከአላህ ሌላ ላለ ማንኛውም ነገር የማያጎነብስ ነው። …
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: