Weight | 456 g |
---|
ኢሕያእ ዑሉሚዲን
$12.00
ኢሕያእ ዑሉሚዲን በዓለማቀፍ ደረጃ ብዙ የተባለለት መጽሐፍ ነው። የአዘጋጁ የኢማም አል-ገዛሊ መታወቂያና መገለጫ ሆኖም ለዓመታት ዘልቋል። በርካታ መጽሐፎችም መጽሐፉን መሠረት አድርገው ተዘጋጅተዋል። በተለያየ መልኩ አጥረውና ተጨምቀው ቀርበዋል። ኢሕያእ በበርካታ ጉዳዮች ዙርያ የሚያተኩር መጽሐፍ ነው፡፡ ከእምነት እስከ ፍልስፍና፡፡ በርካታ አስገራሚ ማብራሪያዎችም አሉት፡፡
መጽሐፉን አሳጥሮ በማቅረብና በማዘጋጀት ረገድ በርካቶች የሞከሩ ሲሆን ለዚህ ትርጉም ሥራ የተመረጠው በአብዛኛው የሷሊሕ አሕመድ አሽ-ሻሚን ዝግጅት ነው፡፡ ከመጽሐፉ የተዘለሉና ጠቃሚ ናቸው ተብለው የታሰቡ መልዕክቶችም ከዋናው መጽሐፍ በመውሰድ ተጨምረዋል።
የገጽ ብዛት ፡ 504
የታተመበት ዓመት ፡ 2010
ከመጽሐፉ ፡
ዕውቀት በራሱ ትልቅ ክብርና ደረጃ አለው። አላህም (ሱ.ወ.) ይህንኑ ተናግሯል። መላእክትና ነቢያትም በተሠጣቸው ዕውቀት ምክንያት የተለየ ክብርን አግኝተዋል።
አንድ ውድ እና ተፈላጊ የሆነ ነገር -ለሌላ ነገር የሚፈለግ፣ ለሱነቱ የሚፈለግ እና ለሁለቱም የሚፈለግ ተብሎ በሦስት ሊከፈል ይችላል። ለሱነቱ የሚፈለግ ነገር ለሌላ ነገር ከሚፈለገው በበለጠ ደረጃ አለው።
ለሌላ ነገር የሚፈለግ ዕውቀት ስንል፡- ለምሳሌ በሱ ምክንያት ወርቅ እና ብር ለማግኘት ማለታችን ነው። እነርሱ ደግሞ ምንም ዋጋ የሌላቸው ድንጋዮች ናቸው። አላህ (ሱ.ወ.) ከሌሎች ድንጋዮች በተለየ መልኩ ዋጋ እንዲኖራቸው አድርጎ በነርሱ ጉዳዮቻችን የማንፈፅምባቸው ቢሆን ኖሮ እነርሱም አፈር ውስጥ እንደሚገኙ እንደሌሎች ድንጋዮችና ኮረቶች በታዩ ነበር።
በሱነቱ የሚፈለግ ነገር ስንል፡- በመጨረሻው ዓለም ስኬትን የሚጎናፅፍ እንዲሁም የአላህን (ሱ.ወ.) ፊት በማየት የሚገኘውን እርካታ የሚያድል ማለታችን ነው።
ለሱነቱና ለሌላም ነገር (ለሁለቱም) የሚፈለግ ስንል ፡- በሰውነት ጤና መሆንና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል። ለምሳሌ አንድ ሰው ጤናማ ሆነ የምንለው ሰውነቱ ከበሽታ ጤና ሲሆን መንቀሳቀስም ሆነ ወደፈለገው ጉዳዩ መሄድ ሲችል እንደማለት ነው።
በዚህም የተነሳ የሦስቱም ዓይነቶች መነሻቸው ዕውቀት ነው። ዕውቀት በራሱ ጣፋጭና አስደሣች ነገር ነው። በሱነቱም የሚፈለግ ነው። ወደ መጨረሻው ዓለም ስኬትና ደስታ የሚያደርስም ነው። ወደ አላህ (ሱ.ወ.) ለመቅረብም በርሱ ዘንድ ለመወደድም የሚያበቃ ነው። አላህ (ሱ.ወ.) ማወቅ የሚቻለው በዕውቀት ነው። አላህን (ሱ.ወ.) በትክክል የሚያውቁት አዋቂዎቹ ብቻ ናቸው።
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት