አድ-ዱዓኡል ሙስተጃብ

3.00 $

በዱዓ ዙርያ በርካታ የተዘጋጁ መጽሐፎች አሉ፡፡ በዚህ መጽሐፍ ዉስጥም የተመረጡ ምርጥ ዱዓዎችና ዚክሮች ተካተዋል፡፡
ዱዓ ዒባዳ ነው፡፡ አላህ ከዱዓ የሚኮፈሱትን ይቆጣል፡፡ ለሁሉም ነገር ዱዓ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ አላህ ዱዓ የሚያደርጉትን ይወዳልና፡፡ “አዱዓኡል ሙስተጃብ” መጽሐፍ በአቀራረቡ እጥር ምጥን ያለ ማንም በየትኛውም ቦታ በዕለቱ ሊገለገልበት በሚችል መንገድ የተዘጋጀ በመሆኑ ከራስ ሊለይ የማይገባው መጽሐፍ ነው፡፡
አዘጋጅ ፡ ሙሐመድ ጧሒር ዘይን
ትርጉም ፡ ሐሰን ታጁ
የገጽ ብዛት ፡ 240
የታተመበት ዓመት ፡ 2002
ከመጽሐፉ ፡ የዱዓ እውነተኛ መገለጫ ከአላህ ፍፁም ከጃይ ሆኖ መገኘት፣ ከምድራዊ ኃይልና ብልሃት ሁሉ ተስፋ ቆርጦ ወይም ፀድቶ ወደርሱ መመለስ፣ የርሱን አቅምና ችሮታ ብቻ ተስፋ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ከዱዓ ሥርዓቶች መካከል- ዉዱእ ማድረግ፣ እጅን ወደላይ ማንሳት፣ ወደ ቂብላ መዞር፣ በዱዓ ቁርጠኛ ሆኖ መለመን፣ ለምላሹ አለመቸኮል፣ ወሰን አለማለፍ … ይጠቀሳሉ ….
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት