አን-ነፊስ (ዐረቢኛ-አማርኛ- እንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት)

445.00 $

የዐረብኛ ቋንቋ በአፍሪካና ኢስያ አህጉራት በሚገኙ አገራት በሰፊው ይነገራል፡፡ ቋንቋው ከ1 ቢለየን በላይ ተናጋሪ እንዳለው ይገመታል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ በዐረብ ሀገራት የተከበበች እንደመሆኗ በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ከሀገር ሀገር የሚሸጋገሩ ዜጐች በቋንቋው ይጠቀማሉ፡፡ የሙስሊሞች መመሪያ የሆነው ቁርኣን ደግሞ በቋንቋ ሰዋሰዋዊ ሥርዓት ሥፋትና ጥልቀት ባለው ዐረብኛ ቋንቋ ነው የወረደው፡፡ እነዚህን ዘርፈ ብዙ እውነታዎች የቋንቋዉን አስፈላጊነት ያመለክታሉ፡፡ አዘጋጁ ከ10 ዓመታት በሆነ ልፋትና ድካም ያሰባሰባቸዉን 18 ሺህ ቃላት ያሉትን ዐረቢኛ አማርኛ እንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት እነሆ አሰናድቷል፡፡ በስዕላዊ መግለጫ በማስደገፍ የቀረቡ ሳይንሳዊ ስያሜዎች፣ የሀገራት ስም፣ ተቀባይነት ያላቸው የተለያዩ ምህፃረ ቃላትና ሌሎችም ጠቃሚ መረጃዎች ከነምሳሌያቸው የተካተቱበት በዓይነቱና በአቀራረቡ ልዩ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ በስስና እና ጠንካራ ሽፋን የተዘጋጀ ነው፡፡

አዘጋጅ፡ ሙስጠፋ ሓሚድ ዩሱፍ
የገጽ ብዛት ፡ 904
የታተመበት ዓመት፡ 2003
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት
ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ!!

Out of stock

Category: