አንዲት ዕለት በጀነት

2.00 $

እነሆ! ይህች በሸይኽ መሕሙድ አል-ሚስሪ የተዘጋጀችው ስለ ጀነት የምታተትና ጀነትን የምታስናፍቅ መጽሐፍ የአማርኛ ትርጉም ናት፡፡ አዘጋጁ ስለ ጀነትና ፀጋዎቿ ሊያጓጓን በሚያስችል መልኩ ከትበዋል፡፡ በጣም እንድናስባት አድርገው ስለው ጀነትን ለኛ አቅርበዋል፡፡ በርግጥ ጀነት በህሊና የማይሳል ዓለም ነው፡፡ ግና ቁርኣንና ሐዲሥን መሠረት ባደረጉ መልዕክቶች የተወሰኑ ሀሳቦች ተላልፈዋል፡፡ የመጽሐፉ ተርጓሚ ዒማዱዲን ዙልፊቃርም መጽሐፏን አሳጥሮ በማቅረብ አበርክቶልናል፡፡ አላህም በመልካም ምንዳዉን ያብዛለት፡፡
ዝግጅት ፡ ሸይኽ መሕሙድ አል-መስሪ
ትርጉም ፡ ዒማዱዲን ዙልፊቃር
የገጽ ብዛት ፡ 128
የታተመበት ዓመት ፡ 2012
ከመጽሐፉ ፡
ጥበበኛው ሐሰን አል-በስሪ “ላ ተጅዐል ሊነፍሲከ ሠመነን ገይረል ጀንነህ!” ይላሉ፡፡ “የአንተነትህን ዋጋ ከጀነት በስተቀር በምንም እንዳትተምነው!” ምክንያቱም የአማኝ ነፍስ ዋጋ ዉድ ናት፡፡
… እናም (ይህች) የምድራዊት ሕይወት ፀጋ እና ተድላ፣ ከኃያሉ የአላህ ፍራቻ የተነሳ ከዐይንህ የምትመነጭን አንዲት ዘለላ እንባ አትስተካከልም!። (የከበረ) አንተነትህን ዋጋ፥ በዚህች ከንቱ ዓለም በሚመነዘር ተመን የሠፈርከው ጊዜ፥ ያኔ ስብዕናህን በርካሽ ሽጠሃል። እነሆ አንተኮ፣ ከወደመብህና ከምትቆዝምበት ሃብትና ንብረት በእጅጉ የላቀ ዋጋ ያለህ ፍጡር ነህ። ሃዘንና ትካዜ የሚገደውማ ፣ ፈሪሃ አምላክ ለጎደለውና የጌታውን ትዕዛዛት ለሚተላለፍ አመፀኛ ሰው ነው። ለምን ቢባል ወደ ጌታህ ጀነት ከመግባትም ሆነ፣ በጀነት ማዕረግ ከመመንደግ የሚያቅቡን (አላህን አለመታዘዝና ደንብና መመርያዎቹን የመጻረር) ተግባራት በመሆናቸው ነው። ስለሆነም አሁንም ደግሜ (አደራ) እልሃለሁ፣ “የአንተነትህን ዋጋ ከጀነት በቀር በምንም እንዳትተምነው!፡፡”
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: