አቡበክር አስ- ሲዲቅ

$10.00

የመጽሐፉ ርዕስ፡ አቡበክር አስ-ሲዲቅ
አዘጋጅ፡ ዶ/ር ዐሊ ሙሐመድ አስ -ሶላቢ
ትርጉም፡ አሕመድ ሁሴን (አቡ ቢላል)
የገጽ ብዛት፡415
ምድር ከተሸከመቻቸው የኢስላም ታላላቅ ስብዕናዎች መካከል አቡበክርን (ረዐ) የሚያህል አልተፈጠረም፡፡ እጅግ ርኅሩኅ፣ አልቃሻ፣ ብልህ፣ በሌላ መልክ ደግሞ ጀግና ብሎም በወሳኝና እጅግ አደገኛ ጊዜያት ዑማውን ለመታደግ ብቃት ተላብሰው የሚገኙ የዘመን ክስተት ናቸው፡፡
ይህ መጽሐፍ ስለ ታላቁ አቡበክር አስ ሲዲቅ የሕይወት ገጽ በስፋት የቀረበበት ነው፡፡ የዚህ መጽሐፍ አዘጋጅ አንጋፋው የታሪክ ባለሙያ በዘርፉ ላይ አንቱ የተባሉት ሸይኽ ዐሊ ሙሐመድ አሰሶለቢ ሲሆኑ ከርካታ የሲራ ስራዎቻቸው መካከል ለሐገራችን ሁለተኛው ነው፡፡ ይህን ስራ ደራሲና ጸሐፊ አሕመድ ሑሴይን ተርጉሞታል፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ በአጠቃላይ ታላቁና የመልእክተኛው ምትክ ስለነበሩት አቡበከርከር ውልደት እስከ ታላላቅ ገድሎቻቸው ስለ እምነት ያደረጉትን መስእዋትነት ከሙሉ አስተምህሮቱ ጋር ለዛሬ ተጨባጫችን ምን እንደሚያበረክት በመዳሰስ በተብራራ ሁኔታ ቀርቧል፡፡
መልካም ንባብ!

Category: