አርባ ዓመት ያልሞላቸው አርባ ዓሊሞች

3.00 $

አላህ (ሱ.ወ.) በቁርኣኑ፤ ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ.) በሐዲሣቸው ውስጥ ዑለሞችን አወድሷቸዋል፡፡ ዑለሞች በምድር ላይ የነቢያት ወራሾች ናቸው፡፡ ሃይማኖታዊ ዕውቀትም ወደ ማህበረሰቡ የሚሰራጨው በነርሱ አማካይነት ነው፡፡ ትልቁ ዕውቀት ዲናዊ ዕውቀት ነው፡፡ አንድ አባት ለልጁ ከሚያወርሳቸው ነገሮች ሁሉ ትልቁና እጅግ ጠቃሚው ሃይማኖታዊ ውርስ ነው፡፡ ዒልም በወጣትነት ሲሆን ያለ ጊዜ ሰውን ያበስላል፡፡ በትንሽ ዕድሜም ከታላላቆች ጎራ ያስመድባል፡፡ ለአንቱታ ሳይደርሱ አንቱነትን ያጎናጽፋል፡፡ በትላልቅ ሰዎች መዝገብ ውስጥም ያስጠራል፡፡ ይህች መጽሐፍ ሃይማኖታዊ ዕውቀትን በመፈለጉ ረገድ በተለይ ለወጣቶች ትልቅ መነሳሳትን ትፈጥራለች፡፡ መጽሐፏ አርባ ዓመት ያልሞላቸው አርባ ዓሊሞችን አካታላች፡፡ በስብስቡ ውስጥ የተካተቱት ስብእናዎች ከሰሓቦች እስከ ታቢዒዮች እና ከነርሱም ቀጥሎ ያሉት ቀደምት ደጋግ ዓሊሞች ናቸው፡፡ ቁምነገሩ ስማቸውንና ዝናቸውን መሸምደድ ሳይሆን ታሪካቸውን በመጠኑም ቢሆን አውቆ እንደነሱ ሁሉ ዓሊም ለመሆን መነሳሳትና የዒልምን ክብር መረዳቱ ላይ ነው፡፡
አዘጋጅ ፡ አልአሚን አልሓጅ ሙሐመድ አሕመድ
ትርጉም ፡ሙሐመድ ሰዒድ
የገጽ ብዛት ፡
የታተመበት ዓመት ፡ 2007
ከመጽሐፉ ፡ 108
ሰዕድ ኢብኑ ሙዓዝ (ረ.ዐ.) እንዲህ ብሏል፡- ‹ሦስት ቦታዎች ላይ ትልቅ ሰው ነበርኩ፡፡ በሌሎች ቦታዎች ላይ ደግሞ እንደማንኛውም ሰው ነበርኩ፡፡ ከአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አንድም ሐዲሥ አልሰማሁም ከአላህ (ሱ.ወ.) የሆነ እውነት መሆኑን በእርግጠኛነት ያመንኩ ቢሆን እንጂ፡፡ በሰላት ውስጥም አልሆንኩም ከሷ እስክወጣ በሷ ብቻ የተወጠርኩ ቢሆን እንጂ፡፡ አንድም የጀናዛ ሽኝት ላይ አልተገኘሁም ሥርአቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ነፍሴ የምትለውንና ሌሎች ሰዎች ስለ ጀናዛዋ የሚሉትን የተቃረንኩ ብሆን እንጂ፡፡›
ታላቁ ታብዒይ ሰዒድ ኢብኑ አልመስየብ (ረሒመሁላህ) ‹የዚህን ዓይነቱን ባህሪ ዓቢድ (አላህን በሚገባ የሚያመልክ ሰው) እንጂ ሌላ ሰው ይኖረዋል ብዬ አላስብም፡፡› ብለዋል፡፡

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: