አል-አዝካር አን-ነወዊ

$11.00

መጽሐፉ በርካታ ጉዳዮችን የሚዳስስ እጅግ ጠቃሚ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ ከአላህ ቀርበን እንድንኖር የሚያግዙን፤ በሕይወታችን ዉስጥ በእጅጉ ሊጠቅሙንየሚችሉ ብዙ ርዕሦችን አካቷል፡፡ የተለያዩ የዕለት ተዕለት ዚክሮችና ከዚክር ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮች በሰፊ ትንታኔ የቀረቡበት ጥልቀት ያለው መጽሐፍ ነው፡፡ አል-አዝካር ከዚክር (የአላህ ዉዳሴ) ዙርያ የተዘጋጁ በርካታ መጽሐፎች እናት ነው፡፡ ብዙ መጽሐፎች የተዘጋጁትም ይህንን መጽሐፍ ማጣቀሻ በማድረግና በማሳጠር ነው፡፡
አዘጋጅ ፡ ኢማም ነወዊ
ትርጉም ፡ ሙሐመድ ሰዒድ
የገጽ ብዛት ፡ 671
የታተመበት ዓመት ፡ ነሐሴ 2006
ከመጽሐፉ ፡
ዚክር በቀልብ አሊያም በምላስ ሊደረግ ይችላል፡፡ በላጩ ግን በምላስ እና በልብ አንድ ላይ ሲደረግ ነው፡፡ ከሁለት አንዱን መምረጥ ግድ ካለ ደግሞ በቀልብ ማድረጉ የተሻለ ነው፡፡ ሪያእ ይሆንብኛል ብሎ በመስጋት በምላስና በቀልብ አንድ ላይ ዚክር ማድረግን መተው ተገቢ አይደለም፡፡ ባይሆን በሁለቱም አንድ ላይ በማድረግ የልዕልና ባለቤት የሆነውን አላህን ውዴታ መፈለግ ይመረጣል፡፡ ፉዶይል ኢብኑ ዒያድ ረሒመሁሏህ ‹ለሰው ብሎ ሥራን መሥራት ሪያእ /ይዩልኝ/ ነው፡፡› ብለዋል፡፡ አንድ ሰው የሌሎችን ትኩረት የማግኘት በር በራሱ ላይ የሚከፍት ከሆነ፤ አሊያም ከመጥፎ ጥርጣሬያቸው ለመጥጠበቅ ብሎ መጠንቀቅ የሚያበዛ እንደሆነ አብዛኛው የመልካም በር መንገድ በተዘጋበት ነበር፡፡ እጅግ አንገብጋቢና ትላልቅ የሆኑ የሃይማኖት ጉዳዮችም ባመለጡት ነበር፡፡ ይህ በርግጥም የአዋቂዎች መንገድ አይደለም፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት