አል- ቀለም

2.00 $

አል-ቀለም ለጀማሪ የዐረቢኛ ተማሪዎች ታስቦ የተዘጋጀ መጽሐፍ ሲሆን በውሰጡም የዐረቢኛ ፊደላትን መሠረታዊ ባሕሪያትና የድምፅ አወጣጥ ስልታቸውን፣ መሠረታዊ የአነባበብ መርሆዎችንና የሰዋሰው ሕግጋትን እንዲሁም ከዕለት ተዕለት ኑሯቸው ውስጥ ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ ተብሎ የታሰበባቸውን ቃላትና ሙሉ ሃሳቦች ተካተዋል፡፡ በተቻለ መጠን የቃላት ክምችታቸውን ማዳበር ይችሉ ዘንድ በዛ ያሉ ቃላትን እንድታቅፍ ተደርጓል፡፡ ቃላት በተቻለ መጠን የቋንቋው ተናጋሪዎችን የድምጽ አወጣጥ ስልት እንዳይለቁ ጥንቃቄ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡
አዘጋጅ፡ አምባሳደር ኡስታዝ ሐሰን ታጁ
የገጽ ብዛት ፡ 160
የታተመበት ዓመት ፡ ህዳር 1991
ከመጽሐፉ ፡ ዐረብኛ ከሴም ቋንቋዎች አንዱ በመሆኑ በፊደላት ድምፅ አወጣጡ፤ ከቃላት አሰካኩ እንኳን ሳይቀር፣ ከእንግሊዝኛ እና ከሌሎች የምዕራቡ ዓለም ቋንቋዎች ይልቅ ለአማርኛና ለትግርኛ ይበልጥ ቀረቤታ አለው፡፡ ዐረብኛ 28 ፊደላት ሲኖሩት “ሑሩፈል ሂጃእ” ይሠኛሉ፡፡ ዐረብኛ ለንባብ የሚረዱ አራት ዋና ዋና ምልክቶች አሉት፡፡ ፈትሕ፣ ዶማ፣ ከስራ፣ ሱኩን ይሠኛሉ ….
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት
ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ!!

Category: