Weight | 248 g |
---|
አል-ሒጃብ
$6.00
ይህ መጽሐፍ ፀረ ኢስላምና ምዕራባዊ ሥርዓትን እየናጡ ያሉትን ቁልፍ ማኅበራዊ ችግሮች እያነሳ ኢስላማዋ መፍትሔዎቻቸውን ይተነትናል፡፡ ኢስላም በሁለቱ ፆታዎች የጐራ ግንኙነትና በሴቶች ማኅበራዊ ደረጃ ላይ ያለውን አቋም አስመልክቶ የተሰራጩ ቅጥፈቶችን ያርማል፡፡ የተዛቡ አመለካከቶችንም ያስተካክላል፡፡ አዘጋጅ ፡ አቡል አዕላ አልመወዱዲ
ትርጉም ፡ ሙሐመድ አማረ እና ኢድሪስ ሙሐመድ
የገጽ ብዛት ፡ 263
የታተመበት ዓመት ፡ 1987
ከመጽሐፉ ፡-
በማናቸውም የሰው ልጅ ላይ ጎልቶ የሚታይ አንድ የጋራ ድክመት አለ። ይኸውም የሕይወት አቅጣጫና ዝንባሌውን በአንድ በተወሰነ ዕይታ ላይ መሠረት ሲያደርግ በቅድሚያ በምርምር ላይ በመመርኮዝ ሳይሆን በጭፍንና ያለምክንያት መሆኑ ነው። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግን አሳማኝ ምክንያቶችን በመደርደር ይህ አመለካከቱ ትክክለኛ መሆኑን ለማሳየት ይጥራል። ሂጃብን በተመለከተ ሙስሊሞች የተጠቀሙበት የአቀራረብ ስልትም ከዚሁ ጋር ተመሳሳይ ነበር። ይህ አመለካከት የመነጨው ሃይማኖታዊ ጠቀሜታ ያስገኛል ወይንም ለሕዝቡ አስፈላጊ ነው ከሚል ስሜት ሳይሆን ይልቁንም በቅኝ ገዢዎች ባህል አድናቆት የመዋጥና እነዚህ ኃይሎች በኢስላማዊ ባህል ላይ የከፈቱት መርዛማ ፕሮፖጋንዳ ውጤት ነው።
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት