ኑ ረሱላችንን እንውደድ

3.00 $

ወደ ነቢያችን የአላህን መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ዉዴታ የሚጣራ መጽሐፍ ነው፡፡ ከዉልደት እስከ ህልፈት የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) የሕይወት ታሪክም በመጠኑ ተዳሶበታል፡፡ መጽፉ የኡስታዝ ኢንጂነር በድሩ ሑሴንን የሲዲ ሥራ መሠረት ያደረገ ነው፡፡
መጽሐፉ በዋናነት ለነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ያለንን ፍቅር ልኬታ ይጠይቃል፡፡ በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሕይወት ያጋጠሙ እውነታዎችን የነበራቸውን ተዓምራት፣ ስብእናቸውን፣ ለሰው ልጆች እና ለፍጡራን የነበራቸውን ፍቅር በንዑስ ርዕሶች እየከፋፈለ ያስነብበናል፡፡ እኛ ተከታዮቻቸው ለነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያለን ፍቅር ምን ያህል እንደሆነም ይጠይቃል፡፡ በመጠየቅ ብቻ ሳይወሰን ለምን ልንወዳቸው እንደሚገባም ምላሹን ይሰጣል፡፡ መጽሐፉ ሲዲውን ለተመለከቱም ሆነ ላልተመለከቱ ጥሩ ግንዛቤን የሚያስጨብጥ ነው፡፡
ቅንብር ፡ ሙሐመድ ሰዒድ
የገጽ ብዛት ፡ 91
የታተመበት ዓመት ፡ ሐምሌ 2002
ከመጽሐፉ ፡ በአሁኗ ሰዓትና ደቂቃ ‘ ማንን ማየት ይመኛሉ አሊያም ይፈልጋሉ ? ’ ቢባሉ ማንን ይመርጣሉ ። ምርጫዎ እጅግ በሚወዱት በሚያደንቁትና በሚያከብሩት ሰዉ ላይ ስለመሆኑ ጥርጥር የለዉም ። ታዲያ እጅግና ከልብ የሚወዱት የሚያፈቅሩትና የሚያከብሩት ማንን ይሆን ? እናትዎን ፣ ፍቅረኛዎን ፣ የኳሱን ንጉስ ሮናልዶን ወይንስ ሌላ… ። በርግጥ ምርጫችን እንደ ኢማናችን ነዉ ። ምኞታችንም እንደ ለነገሮች ያለን ክብደትና ቅለት ነዉ ። የዚህ ዩኒቨርስ ታላቁ ሰዉ ግን ከዛሬ ሺህ ምናምን አመታት በፊት እኔና አንተን አሻግረዉ ይመለከታሉ ። እኔና አንተንም ለማየት ይናፍቃሉ ። ‘ ናፈቁኝ ’ ሲሉም በአደባባይ ይናገራሉ ።
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 99 g