Weight | 166 g |
---|
Moral & Social Issues
ትዳርን የሚያጣፍጡ 1000 መንገዶች
2.00 $
በትዳር ሕይወት ውስጥ የሚከሰቱትን አለመግባባቶች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የምንጠቀምባቸው ዘዴዎችና መንገዶችን ስንቶቻችን እናውቃቸዋለን? የመጽሐፉ ደራሲ በ1000 መንገዶች ትዳርን ማጣፈጥ ይቻላል ይሉናል፡፡ በእስልምና የትዳር ሕይወት እንዴት እንደሚቃኝ፣ የቤተሰብ ማስተዳደር ሒደት ምን መምሰል እንዳለበት ሁሉ መጽሐፉ ይነግረናል፡፡
ዝግጅት ፡ ቡሰይና አስስይድ
ትርጉም ፡ ሙስጠፋ ሐሚድ
የገጽ ብዛት ፡ 168
የታተመበት ዓመት ፡ የካቲት 2001
ከመጽሐፉ ፡
– ፍቅር በትዳር ሕይወት ዉስጥ እጅግ አስፈላጊና አንገብጋቢ ቢሆንም በፍቅር ላይ ብቻ የምትመካ አትሁን፤
– ለራስህ እንደምታስብ ሁሉ ለሚስትህም ቅን አሳቢ ሁን፤ ለራስህ የምትወደዉን ነገር ሁሉ ለሚስትህ ዉደድ፤
– የቤትሽን ሚስጢሮች በተቻለሽ መጠን ጠብቂ፤ ባልሽን በሥራው አበረታቺው፡፡
– ማንኛዉንም ዓይነት አቤቱታዎች ትንሽ ትልቁን ሁሉ ለባልሽ በማቅረብ አታስጨንቂው፤
– ሁለታችሁም አንዳችሁ ሌላኛዉን ለማስደሠት ጣሩ፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት