ተጅዊድ

5.00 $

ቁርኣን የዐረብኛ ቋንቋ ጽሑፍን ማንበብ የቻለ ሰው ሁሉ እንዲሁ በዘፈቀደ የሚያነበው መጽሐፍ አይደለም፡፡ የአላህ ቃል ነዉና ባማረ እና በተስተካከለ መልኩ መነበብ ይኖርበታል፡፡ ይህም የአነባብ ስልት ተጅዊድ ይባላል፡፡ ቁርኣንን በትክክል ያልተነበበ እንደሆነ ትርጉሙ ይዛባል፡፡ ይህ መጽሐፍ ቁርኣንን አሳምሮ እንዴት ማንበብ እንደሚቻል ያስተምራል፡፡
አዘጋጅ ፡ ሙከሚል ከማል (አቡ ተስኒም)
የገጽ ብዛት ፡ 176
የታተመበት ዓመት ፡ 2012
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

ከመጽሐፉ
ጅዊድ የተሠኘው የእውቀት ዘርፍ በታላላቅ ዑለሞች በኩል ከተውልድ ትውልድ ሲተላለፍ ወደኛ የደረሠ ነው፡፡ ቀደምት ዑለሞች የተጅዊድ ዕውቀትንና መሠረታዊ የቁርኣን አነባብ ሥርዓት ህግጋትን አስቀምጠዉልን አልፈዋል፡፡  የተጅዊድ ትምህርት ዋና ዓላማ ቁርኣን በሚነበብበት ጊዜ ምላስ ስህተት ላይ እንዳይወድቅ መጠበቅ ነው፡፡ የቁርኣን አነባብ ሥርዓት ሕጎች ቀለል ባለ እና አጠር ባለ መልኩ እንደሚከተለው በቅደም ተከተል ቀርበዋል፡፡ ….

Category: