ተዓምራዊ ፈውስ

2.00 $

አላህ (ሱ.ወ.) በምድር ላይ ለተፈጠሩ በሽታዎች በሙሉ መድኃኒት በምድር ላይ ፈጥሯል፡፡ ነቢያችንም (ሰ.ዐ.ወ.) “አንድም በሽታ አልተፈጠረም መድኃኒት ያለው ቢሆን እንጂ፡፡” ብለዋል፡፡ ሰው የትም ቢኖር በሽታ ሳያገኘው የሚኖር አይደለም፡፡ ለሁሉም በሽታ መድኃኒት የመኖሩን ያህል መድኃኒቱን ለመጠቀም ደግሞ እውቀት ይጠይቃል፡፡ የዚህ መጽሐፍ አዘጋጅም የሰዎችን ችግር ለመቅረፍ “ጥቁር አዝሙድ፣ ማር፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ቀይ ሽንኩርት…” ያላቻው አስታዋጽኦ በቀላሉ የሚገመት አይደለም በማለት ጥቅማቸዉን ይዘረዝራሉ፡፡
አዘጋጅ ፡ አቡልፊዳእ ሙሐመድ ዒዘት ሙሐመድ ዓሪፍ
ትርጉም ፡ ዐብደላ ሙሐመድ ዐሊ
የገጽ ብዛት፡ 64
የታተመበት ዓመት ፡ ነሐሴ 1996
ከመጽሐፉ ፡ ከሰው ልጅ ሁሉ ምርጡ የሆኑት፣ የሰብዓኢ ፍጡራን ሁለንተናዊ ሐኪም፣ የአላህ ባል ታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) ጥቁር አዝሙድን ተኣምራዊና ሁለገብ ተፈጥሮ በአጭር ሀረግ ግን ደግሞ ገላጭ በሆነ መልኩ የሠጡትን አስተምህሮ ያላንዳች ጥርጣሬ መቀበል ይገባል፡፡ “ይህች ፍሬ አትለያችሁ፤ በዉስጧ ከሞት በስተቀር ለበሽታዎች ሁሉ ፈውስ ይዛለችና፡፡” ብለዋል …
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: