Weight | 62 g |
---|
ተውበት ማድረግ እፈልጋለሁ ነገር ግን …
2.00 $
በዲኑ መንገድ ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ በአላህ መንገድ መጽናት ይፈልጋሉ፡፡ የራቁትም ቢሆኑ ተመልሰው እውነተኛ የአላህ ባርያ መሆን ይመኛሉ፡፡ እርግጥ ነው ከአላህ መንገድ የራቀ ሰው በዱንያ ጭንቀት ይዋጣል፡፡ በጥፋት ማዕበል ይዋዥቃል፡፡ ታድያ መቼም ይሁን መቼ ወደ አላህ (ሱ.ወ.) ከተመለሰና እጁን ከሠጠ ዳግመኛ ፊቱን ወደ ጥፋት አያዙር እንጂ አላህ ሊምረው ይችላል፡፡ በመንገዱም ላይ ያፀናዋል፡፡ ይህ መጽሐፍ ተውበት በማድረግ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ኃጢኣትን አቅልሎ መመልከት ስለሚያስከትለው አደጋ፣ ስለ ተውባና ምንነቱ፣ ተውባ ለማድረግ እንቅፋት ስለሆኑ ነገሮችና ሌሎችም የተዳሰሱበት ነው፡፡
ዝግጅት ፡ ሸይኽ ሙሐመድ ሷሊሕ አልሙነጂድ
ትርጉም፡ አወል ኸድር
የገጽ ብዛት ፡ 56
የታተመበት ዓመት ፡
ከመጽሐፉ ፡ ተውበት ብታደርግም የበፊት ሕይወትህ ሲታወስህ “በርካታ ኃጢአቶችን እፈፅም ነበር። አሁን ወደ አላህ ምሕረት ተመልሼያለሁ። የሰራኋቸው ኃጢአቶች ግን ዛሬም ትዝ እያሉኝ አዕምሮዬን ሰላም ነስተውታል። እንቅልፍም ሆነ እረፍት ያሳጡኛል። ከዚህ ዓይነት መረበሽ፣ ጭንቀትና መጥፎ ትውስታ እንዴት እገላገል ይሆን?” ለምትለው ተውበት አድራጊ ምላሼ “ይህ ስሜት ለኃጢአቶችሁ ከልብህ ተውበት ለማድረግህ ማስረጃ መሆኑን ያመለክታል” የሚል ነው። የዚህ ዓይነት አዋኪ ስሜት በመሠረቱ ጸጸት ነው። ፀፀት ደግሞ በራሱ ተውበት ነው። ያለፈ ሕይወትህን መቃኘት ያለብህ አላህ ይምረኛል በሚል ተስፋ ይሁን።
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት