Weight | 85 g |
---|
Tawheed
ተውሒድ ይዘቱ እና ሚናው
2.00 $
ተውሒድ የሰው ልጆች የመፈጠር ዋንኛ ዓላማ ነው፡፡ አላህን በብቸኝነት ማምለክ፡፡ ይህም የኢስላማዊው ዐቂዳ (እምነት) አስኳል፤ የኢስላም ትልቁ መሠረት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ አጀንዳ በየዘመናቱ በተነሱ ዓሊሞችና ሊቃውንት በስፋት ሲደሰሱ ቆይቷል፡፡ ከዘመናችን ሊቆች አንዱ የሆኑት አዘጋጁ ይህን ርዕስ ጉዳይ እጅግ ማራኪ፣ ቀላልና ጥልቅ በሆነ አቀራረብ በግሩም ሁኔታ ዳሰውታል፡፡ የመጽሐፉ ተርጓሚም በቀላልና ግልጽ በሆነ አማርኛ አቅርቦታል፡፡
አዘጋጅ ፡ ፕ/ር ኢማም ዩሱፍ አልቀርዷዊ
ትርጉም ፡ ኡስታዝ ሐሰን ታጁ
የገጽ ብዛት ፡ 80
የታተመበት ዓመት ፡
ከመጽሐፉ ፡ በአላህ ማመን የእምነቶች ሁሉ መሠረት ነው፡፡ ሌሎች ነገሮች የርሱ ተቀጥላዎች የርሱ ተከታዮች ናቸው፡፡ በአላህ ካመንክ በኋላ በተያያዥነት በመላእክቱ፣ በመፃህፍቱ፣ በመጪው ዓለም እርሱን በመናኘት፣ በምርመራው ቀን፣ በጀነትና ጀሀነም፣ በሱ የቀደመ ፍርድና ዉሳኔ (ቀዷና ቀደር) ሁሉ ታምናለህ፡፡ በነኚህ ሀሉ ነገሮች ማመንህ በአላህ ከማመንህ የሚመነጭ፤ በርሱም ላይ የታነፀ ነው፡፡ …
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት