ተክፊር

12.00 $

ተክፊር ማለት አንድ ሙስሊም የሆነን ሰው ማክፈር/ ከእስልምና ማስወጣት/ ማለት ነው፡፡ በአንድ ወቅት የዚህ ዓይነት አመለካከት በሀገራችን የማቀንቀን ሁኔታ ተጀምሮ ነበር፡፡ መነሻውም ኢስላምን በጥልቀት አለማወቅ ነው፡፡ ነገሩ በርግጥም አሳሰቢ ነበር፡፡ ስለሆነም ብዥታን ለማጥራት ሲባል ይህን ጉዳይ መዳሰሱ ግድ ሆነ፡፡ አንድ ሰው እንዴት ወደ ኢስላም ይገባል? ኢስላማዊ ተግባሩስ ምንድነው? ከኢስላም ውጭ የሚያሰኘውስ ምን ምን ሥራዎቹ ናቸው? የሚሉትን ጥያቄዎች በመዳሰስ በርካታ መጽሐፍትን በማገላበጥ ደራሲው ይህንን በአስተምህሮቱ የዳበረ መጽሐፍ አዘጋጅቷል፡፡
ዝግጅት ፡ አምባሳደር ኡስታዝ ሐሰን ታጁ
የገጽ ብዛት ፡ 193
የታተመበት ዓመት ፡ መስከረም 1995
ከመጽሐፉ ፡ ቁርኣንና ሐዲሥን ስንመረምር የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሕይወት ዉሎ ስናጠና፣ የሰለፎችን ቃልና ተግባር ስንፈትሽ አንድን ግለሰብ እንደሙስሊም ለመቀበል ከሚያገለግሉ ሸሪዓዊ መስፈርቶች መካከል – ሸሃዳን በቃል መመስከር፣ ሸሃዳን ሊያመለክት የሚችል ቃል ወይም ተግባር መፈፀም፣ ከሙስሊም ቤተሰብ መወለድና የመሣሠሉት ናቸው…
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Out of stock

Category: