Weight | 96 g |
---|
ተቅዋ የአማኞች ስንቅ
$3.00
አላህ (ሱ.ወ.) እሱን መፍራት (ሰንቁ) ተቅዋ የሰው ልጅ የህይወት ትልቁ ስንቅ እና የአምልኮ ተግባራት ሁሉ አስኳል መሆኑ የተዳሰሰበት፡: መጽሐፉ ስለ ተቅዋ (ጥንቁቅነት) ምንነት፣ ወደ ተቅዋ ስለሚወስዱን መንገዶች፣ ራስን ስለመመርመር፣ ነገሮችን ስለማሳመር፣ ስለ ሐያእ፣ ስለ ጽድቅ ነገሮችና ስለ ሌሎችም የተብራራበት ነው፡፡
ዝግጅት ፡ አቡ መርየም መጅዲ ፈትሕ አል-ሰይድ
ጥንቅር ፡ አሕመድ ሑሴን (አቡ ቢላል)
የገጽ ብዛት ፡ 96
የታተመበት ዓመት ፡ መስከረም2006
ከመጽሐፉ : ብዙዎች ተቅዋን በተለያየ መንገድ ገልፀዉታል …
ተቅዋ ማለት አላህ ካዘዘህ ሥፍራ እንዳያጣህ፤ ከከለከለህ ቦታ አለመገኘትህ ነው፡፡
ዐሊ ኢብኑ አቢ ጧሊብ (ረ.ዐ.) ስለ ተቅዋ ሲናገሩ “ኃያሉን አላህን መፍራ፣ ባወረደው ሁሉ መሥራት፣ በጥቂት መብቃቃትና ለመጪው ዓለም መዘጋጀት ነው፡፡” ብለዋል፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት