Additional information
Weight | 216 g |
---|
5.00 $
በሙስሊሞች ምድራዊ ሕይወት ከምናገኛቸው ሥራዎች አንዱ የቢዝነስ መስክ ነው፡፡ በዓለም ላይ ለሚኖሩ ሙስሊሞች ብቻ ሳይሆን ሙስሊም ላልሆኑ ህዝቦችም ጭምር ፍትሃዊ ግብይትን በማሳያት ኢስላማዊ የቢዝነስ ሥነ-ምግባር ሚናው ከፍተኛ ነው፡፡
በብዙ መልኩ ከተንሰራፋው የካፒታሊስታዊ ግለኛ የግብይት ፍልስፍና ጋር በተያያዘ ጥቂት የማይባሉ ሙስሊም ነጋዴዎች አላህ በምድር ወኪል አደርጎ ያመጣቸው የፍትህ ኃዋርያት መሆናቸውን የዘነጉ ይመስላል፡፡ የሚያጋጥሟቸውን ስነ-ምግባራዊ ፈተናዎች በጽናት ከማለፍ ይልቅ በቀላሉ ሲደናቀፉ እናያለን፡፡
በዚህ መለስተኛ ጥራዝ ውስጥ ስለቢዝነስና ኢስላማዊ መገለጫው ጠቃሚ መንደርደሪያዎች ቀርበዋል፡፡ በተለይ ከሥነ-ምግባር ስልጣኔ ጋ በተያያዘ ጥልቀት ያለው ዳሰሳ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡
ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች ከትርፍም አንፃር ቢሳተፉባቸው መልካም ይሆናሉ በተባሉ አማራጮችም ላይ ጥቆማ ተደርጓል፡፡ በተለይ ለሙስሊሞች ጠቀሜታ ያላቸውን ግብዓቶች በማሟላትም ጭምር አትራፊ ቢዝነስ ስለሆኑ አማራጮች ተዳሷል፡፡ ረጋ ባለ መንፈስ ሀሳቦቹን በመቃኘት ከመጽሐፉ ፍሬዎችን ማጣጣም እንደሚቻል ይታመናል፡፡
አዘጋጅ ፡ ሙሐመድ ዐሊ (ቡርሃን)
የገጽ ብዛት ፡ 232
የታተመበት ዓመት ፡ ጥቅምት 2007
ከመጽሐፉ ፡
ዐብዱረሕማን ቢኑ አውፍ ዘካን ለመስጠት አልነበረም ጭንቀቱ… የርሱ ሃብት አስፈላጊ ሆኖ ሳይሠጥ የቀረበት ጊዜ ካለ ያ ነበር የሚያሳስበው፡፡ በዚህ ዘመን ሚስኪኖችን በአደባባይ አሰልፎ አምስት አምስት ብሮች እየሰጡ ለማባረር ብዙ ከፍና ዝቅ የሚያደርጉ ባለሀብቶች ቁጥር ጥቂት የማይባሉ ናቸው፡፡ ሁላችንም እንደየሥራ መስካችን የሚጠብቅብን ኢስላማዊ ኃላፊነት እንዳለ እሙን ነው፡፡
ይበልጥ በንግድ ዘርፍ ላይ የተሰማራን ወይም የምንሰማራ ሰዎች ደግሞ እንላበሰው ዘንድ አላህ ከኛ የሚጠብቅብን ግዴታ ላቅ ያለ መሆኑን ይረዷል፡፡ እነሆ ነጋዴ ስለታላቅ የማህበረሰብ መረጋጋት የሚሰራ ትጉ ሰው ነውና ነብዩ ሙሐመድም(ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) አወድሰውታል…፡፡ “እውነተኛ ነጋዴ (የቢዝነስ ሰው) በትንሳኤ እለት (ደረጃው) ከነቢያትና ፃዲቆች ጋር ይሆናል” በማለት
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት
Weight | 216 g |
---|