ቢስሚከ ነሕያ (አላህ ሆይ በስምህ እንኖራለን)

6.00 $

በአላህ ሥሞች ዙርያ አስደናቂ ትንታኔዎች እና የተለዩ እይታዎች የቀረቡበት ነው፡፡ መጽሐፉ ከአላህ (ሱ.ወ.) ሥሞችና ባህሪያት አንፃር ከዚህ ቀደም ያላየናቸውን በርካታ እይታዎችንና ነጥቦችን ያሳየናል፡፡ አላህን (ሱ.ወ.) ይበልጥ እንድናውቅም ዕድል ይሰጠናል፡፡ የረሳነውን ያስታውሰናል፡፡ ፈጽሞ ያላስተዋልነውንም መንገድም ይጠቁመናል፡፡ የተሰጡት ትንተናዎች የአላህን ሥሞችና ባህሪያት ከመፍራት ይልቅ እንድናፈቅራቸው የሚያደርጉን ናቸው፡፡ ከመሸሽና ከመራቅ ይልቅ በድፍረት እንድንቀርብ የሚጋብዙ ናቸው፡፡
አዘጋጅ ፡ ዐምር ኻሊድ
ትርጉም ፡ ሙሐመድ ሰዒድ
የገጽ ብዛት ፡ 396
የታተመበት ዓመት ፡ 2007
ከመጽሐፉ ፡
አላህ ሆይ! በስምህ እንኖራለን! … ሀያሉንና የተከበረውን አላህን ማወቅ የጠፋ ሕይወታችንን ለመመለስ የምንጠቀምበት አማራጭ የሌለው መንገድ ነው፡፡ የአላህን ስሞች ከነጥልቅ ትርጉማቸው በማወቅ የኢማን ጥማችንን ልንወጣ ይገባል፡፡ የአላህ መልካም ስሞችን በጥልቀት የተረዳን እንደሆነ ከውስጣቸው የሚወጣው ብርሃን ሕይወትን በአዲስ መልኩ እንድንኖር ብርታትና ሀይል ይሆነናል፡፡›
ኃያሉና የተከበረው አላህ (ሱ.ወ) ‹አል-ዐሊም› /እጅግ አዋቂ/ ነው፡፡ ‹አል-ዐሊም› በሆነው በአላህ ስም እንኖራለን፡፡ በዕውቀት እንኖራለን፤ መሃይምነትን ፈጽሞ አንቀበልም፡፡
ኃያሉና የተከበረው አላህ (ሱ.ወ) ‹አር-ረሒም› /እጅግ አዛኝ/ ነው፡፡ ‹አር-ረሒም› በሆነው በአላህ ስም የእዝነት ህይወት እንኖራለን፡፡ ጭካኔን መንገዳችን አናደርግም፡፡
ኃያሉና የተከበረው አላህ ‹አል-ከሪም› /እጅግ ቸር፤ የተከበረ/ ነው፡፡ ‹አል-ከሪም› በሆነው በአላህ ስም ቸርነትና ክብር የተሞላበት ሕይወት እንኖራለን፤ ስስትን አንወድም፡፡
ኃያሉና የተከበረው አላህ ‹አል-በዲዕ› /ከምንም ያስገኘ/ ነው፡፡ ‹አል-በዲዕ› በሆነው በአላህ ስም የምድር ላይ ሕይወታችን በፈጠራ ሥራ ላይ ተሰማርተን እንኖራለን፡፡ ኋላቀርነትን በጀ አንልም፡፡
ኃያሉና የተከበረው አላህ አል-ዐዚዝ /እጅግ አሸናፊ/ ነው፡፡ አል-ዐዚዝ በሆነው በአላህ ስም የክብር ሕይወት እንኖራለን፡፡ ሽንፈትን ፈፅሞ አንፈቅድም፡፡

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 365 g