ቡና በገመና

2.00 $

ሥነ-ግጥም ከሌሎች የሥነ-ጽሑፍ ዓይነቶች ለየት የሚልበት ነጥብ በርካታ ሃሳቦችን አጠርና ጠቅለል ባለ ሓሳብ እንዲሁም ውብና ባማረ ቋንቋ ማስቀመጡ ነው፡፡ ይህ የግጥም መጽሐፍ የቋንቋ ምጥቀቱ፣ የስንኝ አወቃቀሩ፣ የቃላት ምጣኔ፣ ዜማዊነቱ፣ ከምንም በላይ ደራሲው በሃይማኖታዊ ታሪክ ላይ ያለው የበሰለ እውቀት መጽሐፉን ተወዳጅ እንዲሆን አድርጐታል፡፡
ዝግጅት ፡ ኢማዱዲን ዙልፊቃር
የገጽ ብዛት ፡ 96
የታተመበት ዓመት ፡ የካቲት 2004
ከመጽሐፉ ፡
ከቅን ሥራ አኳያ – ላለን መነሳሳት
ሶስት ሰበብ አለ – ባይነኝ ባልሳሳት
አንደኛው ለአላህ – ሁለት ለሰው ሲባል
ሶስተኛው ለራስ – በሚል ይመደባል
እናም ሰለፎቹ – የተቀደሙቱ
ሦስተኛዉን ገድፈው – ዳኑ በሁለቱ
ለራሣቸው ሲሉ – ለአላህ እየሞቱ፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: