ቡሉጉል መራም የአማርኛ ትርጉም ቅጽ 1

$10.00

በሙስሊሙ ዓለም እጅግ በስፋት ከተሠራጩ መጽሐፎች መካከል አንዱ ነው፡፡ በተለይ የፍቅህ ዘርፍ ተማሪዎች በቂርኣት ክፍ እያሉ ሲሄዱ ለመማርና ለመመራመር ከሚመርጧቸው ተወዳጅ መጽሐፎች መካከል ይመደባል፡፡ መጽሐፉ ሰፋ ካለ ማብራሪያ ጋር በሁለት ቅፆች የተዘጋጀ ሲሆን ከ1400 በላይ ሐዲሦች ተካተዉበታል፡፡ በአምስቱ የእስልምና ማዕዘናት፣ በማኅራዊ እና ግላዊ፣ እዲሁም በዕለት ተዕለት ኑሯችን፣ ዙርያ፣ ከትልቅ እስከ ትንሽ የተለያዩ ኢስላማዊ ድንጋጌዎች፣ ብይኖችና አስተምህሮዎች በስፋት ያገኙበታል፡፡
አዘጋጅ ፡ ኢብኑ ሐጀር አል-ዐስቀላኒ
ትርጉም ፡ ኡስታዝ አምባሳደር ሐሰን ታጁ
የገጽ ብዛት ፡ ቅጽ አንድ ፡ 506 ቅጽ ፡ 508
የታተመበት ዓመት ፡ 2008/2009
ከመጽሐፉ ፡
ኢስላም ገርና ቀላል ሃይማኖት ነው፡፡ የተለያዩ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት ለተከታዮቹ የተለዩ ድንጋጌዎችን አስቀምጧል፡፡ ከነዚህ መሐል በጉዞ ላይ ያለን ሰው (ሙሳፊር) እና በሽተኛን የተመለከተ ድንጋጌዎች ናቸው፡፡ በጉዞ ላይ ያለ ሰው ባለ 4 ረከዐህ የግዴታ ሰላቶችን ወደ ሁለት አሳጥሮና ሁለት ወቅት ሰላቶችን በአንድ አዳብሎ እንዲሰግድ ተፈቅዶለታል፡፡በሽተኛም እንደዚሁ ያለበትን ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ የአሰጋገድ ስልት ተመቻችቶለታል፡፡ ለበሽተኛና በጉዞ ላይ ላለ ሰው የተዘረጋው ይህ የአሰጋገድ ሥርዓት የእስልምናን ገርነት ከማሳየቱ በተጓዳኝ ሰላት ክብደት የተሰጠው ዒባዳ መሆኑን ያመለክታል፡፡

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: