በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) የታነፁ ታዳጊዎች

2.00 $

እስልምና ለልጆች አስተዳደግ ትልቅ ትኩረት የሚሠጥ ሃይማኖት ነው፡፡ ልጆች ከትንሽነታቸው ጀምሮ ትልቅ መልካም ዓላማ ኖሯቸው ያንን ዓላማ ለማሳካት፣ ለዚያ ዓላማ እንዲሠሩና እንዲኖሩ ያበረታታል፡፡ ይህ ሁሉ ሊሳካ የሚችለው በኢስላም ጥላ ሥር ነውና ልጆችን ያለመታከት ማስተማርና መንገድ ማሳየት ያስፈልጋል፡፡ በዚህች ትንሽዬ መጽሐፍ ዉስጥ ሶሓቦች የሆኑ ምርጥ የሆኑ የ15 ትናንሽ ልጆች ታሪክ ተካቷል፡፡ ልጆቹ በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ዙሪያ በማደጋቸው ምንም እንኳን በዕድሜ ትንሽ ቢሆኑም በርሣቸው እነፃ እና አስተምህሮ ምክንያት በልጅነታቸው ትልቅ ሆነዋል፡፡ ካደጉ በኋላም ቢሆን ያ የልጅነት እርሾ ጠቅሟቸው፣ ያንኑ መንገድ ሳይለቁ በመጓዛቸው ለሙስሊሙ ማኅበረሰብና ለኢስላም ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ የዚህ መጽሐፍ ዓላማ ልጆች ከቀደመው ደጋግ ትውልድ ታሪክ ተምረው የትልቅ ዓላማና የመልካም ሥነምግባር ባለቤት ሆነው እንዲያድጉ ነው፡፡ ትልቅ ሆኖ የተወለደ ሰው የለም፡፡ ሁላችንም በሂደት ነው ወደ ትልቅነት የመጣነው፡፡
ትርጉም ፡ ሙሐመድ ሰዒድ
የገጽ ብዛት ፡ 88
የታተመበት ዓመት ፡ 2012
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 94 g