በሃይማኖት ማስገደድ የለም

7.00 $

የሁለት ደራሲዎች ምር የምርምር ውጤት የሆነው ይህ መጽሐፍ ኢስላም የሰው ልጆችን የእምነት ነጻነት ምን ያህል በወጉ እንደሚጠብቅና እንደሚያስጠብቅ በሚገባ ከማስቀመጡ በተጨማሪ በኢስላም ሃይማኖት የሰው ልጆችን ነጻ ፍላጐት በመጨፍለቅ፣ የሰው ልጆችን በኃይል በማስገደድ ኢስላምን እንዲቀበሉ የሚያደርግ ፖሊሲ እንደሌለ የተለያዩ ክስተቶችንና ማስረጃዎችን በማጣቀስ ያረጋግጣል፡፡
በርግጥም ኢስላም የሰዉን ልጅ ነፃ ፍላጎቱን የጠበቀ ሃይማኖት ነው፡፡ በሃይማኖት ዉስጥ ማስገደድ የሌለ ስለመሆኑ፣ ስለ ኢስላም መሰረታዊ ትርጓሜ፣ መርሆና ባህሪያቱ፣ ሰብዓዊ መብቶች በኢስላም፣
ከማል ኽይረዲን እና ሙስጦፋ ሐሚድ
የገጽ ብዛት ፡ 301
አዘጋጅ ፡ ኸማል ኸይረዲን እና ሙስጦፋ ሐሚድ
የገጽ ብዛት ፡ 301
የታተመበት ዓመት ፡ ሚያዚያ 2004
ከመጽሐፉ ፡ የተባበሩት መንግሥታት ቻርተርና ብያኔዎች እንዲሁም ሕግጋት እና ደንቦች ከአላህ የተለገሱ ከሆኑት መብቶች ጋር ፈጽሞ ሊወዳደሩ እንኳ አይችሉም። ምክንያቱም የመጀመሪያው የዓለም መንግሥታቱን ቻርተር ከፈረሙት ባሻገር ( ውጭ) በሁሉም ላይ ተፈጻሚ መሆን የማይችል ሲሆን ከአላህ የተለገሱት መብቶች ግን ለምዕመናን (በኢስላም ጥላ ሥር ለተሰባሰቡት) ሁሉ ያለማንም ጣልቃ ገብነትና ተጽዕኖ ተፈጻሚ ናቸው። እነዚህ ሰብአዊ መብቶች የኢስላም ሃይማኖት አንድ አካል ናቸው። እያንዳንዱ ሙስሊምም ሆነ ሙስሊም ነን የሚሉ አስተዳደሮች ሊቀበሏቸውና እውቅና ሰጥተው ተግባራዊ ሊያደርጓቸው ይጠበቅባቸዋል። ከነኚህም ሰብዓቲ መብቶች መካከል አንዱ በሃይማኖት ማስገደድ የሌለ መሆኑ ነው፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: