ቃሩን እና ዙልቀርነይን

1.00 $

ነብዩላህ ሙሳ (ዐ.ሰ) አላህ ድንቅ ተዓምራትን አስይዞ የላካቸው ታላቅ ነቢይ ናቸው፡፡ በዘመናቸው በሁለት ኃያላን ተሰቅዘው ተይዘው ነበር፡፡ የምድርና ሰማይ ገዥ እኔ ነኝ ብሎ በሚፎክረው ግብጻዊው ፈርኦንና የደለበ ሃብት ባካበተው የሀገራቸው ልጅ አይሁዳዊው ቃሩን፡፡ ቃሩን ለሕዝቦቹ ደንታ የሌለው፣ ፊርአውንን በመጠጋት ሃብት ያካበት፣ ሃብቱም በትዕቢት እንዲወጠር ያደረገው ሰው ነበር፡፡ ይህ መጽሐፍ ስለቃሩን ታሪክ የሚያወሳ ነው፡፡ ለልጆች በሚሆን አቀራረብ ተዘጋጅቷል፡፡
መጽሐፉ የዐማርና ሙናን ከአያታቸው ጋር ምልልስ የያዘ ነው፡፡ መጠያየቃቸው እንደቀጠለ ነው፡፡ አያትየውም ያለፉ ሕዝቦችንና ነቢያትን ታሪክ መንገራቸውን አላቆሙም፡፡ ዙልቀርነይን ገና በልጅነት በአላህ በመታገዝ ጥቂት ሰዎችን ብቻ ይዞ ሀገሩን ከወራሪ እጅ ያስለቀቀ፤ ዙል ቀርነይን (የሁለት ቀንድ ባለቤት) የሚለዉን ስሙን ያገኘውም ሕልሙን የፀሐይን ቀንድ እንደጨበጠ በመናገሩ ነው፡፡ በእድ አምላኪዎችን አላህን እንዲገዙ ማድረግ ያስቻለ ታላቅ ሰው ነበር፡፡ ይህ በቁርኣን ሱረቱል ካህፍ ታሪኩ የተነገረለት ጀግና ለልጆች በሚመች መልኩ በዚህ መጽሐፍ ተተንትኗል፡፡
ቅንብር ፡ ሐሚድና ሱለይማን
የታተመበት ዓመት ፡ ጥቅምት 2003
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: