Weight | 126 g |
---|
ቁድረቱሏህ
3.00 $
የመጽሐፉ ይዘት፡ – ጥልቅ ማስተንተንን የሚጠይቁና ለኢማን የሚጋብዙ እጅግ አስደናቂ የአላህ ሱ.ወ. ተዓምራዊ አፈጣጠሮችን የሚስዳስሰን መጽሐፍ ነው፡፡ የኃያሉ አላህን ልቅና እና ችሎታ የሚያረጋግጡ በርካታ የቁርኣን አንቀጾች በቁርኣን ውስጥ ይገኛሉ አላህ ምድርን መፍጠሩና በራሷና በፀሐይ ዙሪያ እንድትሽከረከር ማድረጉ የቀንና የለሊትን ጊዜያቸውን ጠብቀው እንዲፈራረቁ ማድረጉ ሰማይን ካለ ምሰሶ መዘርጋቱ ሌሎችም የኃያልነቱ የብቸኛ የችሎታ ባለቤት መሆኑን የሚያሳይ ነው ይህና ቀጣዩ ቅጽ 2 መጽሐፍ ይህንኑ የአላህን ድንቅ ችሎታ የሚያሳይ ነው፡፡ ከአርዕስቶቹም መካከል፡- አስደማሚው የዶልፊን አፈጣጠር፣ የአራዊት የማንቀላፋት ሚስጢር፣ ፍጥረታትና የልጆች አንክብካቤ፣ ታላቁ ጉማሬ፣ ልጅ አባቱን ባይመስልም፣ በርግጥም ድንቅ ሆነን ተፈጥረናል፣ ሥጋ በሎቹ ነፍሰገዳይ ተክሎች፣ የሰማይ ላይ ካርታዎችና ከዋክብት፣ ማር የንብ ተዓምራዊ ውጤት፣ ከሰማይ አካላት የተደቀኑ አደጋዎች እና ሌሎችም….ተካተውበታል፡፡
ጥንቅር ፡ አሕመድ ሑሴን (አቡ ቢላል)
የገጽ ብዛት ፡ 131
የታተመበት ዓመት ፡ 2002
ከመጽሐፉ በጥቂቱ ….
በኩላሊትህ ውስጥ የሚገኙ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ኩለቴዎች ያለ አጉሊ መነጽር የማይታዩ ቢሆኑም እንኳ የሚያከናውኑት ተግባር ግን እጅጉን የሚያስደንቅ ነው፡፡ በዚሁ አሠራራቸው ሁለቱ ኩለቴዎች ወደ አምስት ሊትር የሚጠጋ የውሃ ይዘት ያለውን መላውን ደም በየ45 ደቂቃው ያጣራሉ፡፡ የተለያዩ ንጥረነገሮች እንደገና ወደ ሰውነት እንዲገቡ ከተደረገና ብዙዎች ሂደት ከተጠናቀቁ በኋላ አንድ ጤናማ የሆነ አካል በ24 ሰዓት 2 ሊትር ገደማ የሚሆን ቆሻሻ በሽን መልክ ያስወግዳል፡፡ ኩላሊት ራሱን በራሱ የሚያፀዳና የሚጠብቅ አካል ክፍላችን ነው፡፡ …..
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት