ቁርኣንን አስተንትኖ የማንበብ መንገድ

3.00 $

ቁርኣን የሰው ልጆች ሁሉ የሕይወት መመርያ ነው፡፡ ለማንበብ ብቻ የሚነበብ ተራ መጽሐፍ አይደለም፡፡ ወደ ተግባር መለወጥ ያለበት መጽሐፍ ነው፡፡ ምልከታው በዚህም ሆነ በመጨረሻው ዓለም ለስኬት የሚያበቃ ነው፡፡ ጊዜ ወስዶና አስተንትኖ ያነበበ ትልቅ ትምህርት እና ቁምነገር ያገኝበታል፡፡ ማስተንተን የከበደበት ዘመን ላይ ነው ያለነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ቁርኣንን አስተንትኖ ስለማንበብና ስለመረዳት ጠቃሚ ምልከታዎች የሰፈሩበት ነው፡፡
ዝግጅት፡ ፕሮፌሰር ሒክመት ኢብን በሺር ያሲን
ትርጉም ፡ ጁነይድ ዐብዱልመናን
የገጽ ብዛት ፡ 87

የታተመበት ዓመት ፡ ሰኔ 2007
ከመጽሐፉ ፡ ቁርኣንን በጥልቀት ማስተንተን (ተደቡር) በዕለታዊ ሕይወታችን ውስጥ ቅድሚያ ከምንሰጣቸው ነገሮች መካከል ነው፡፡ ምክንያቱም ቁርኣንን እያስተነተኑ ማንበብ በታላቁ ፈጣሪ አላህና በዋና ፍጡራኑ ሰው እና ጂን መካከል የሚደረግ ውይይት በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ምክክር የሚደረግበት መንገድ ደግሞ ታላቁ ቁርኣን ነው፡፡ የአላህን መመሪያዎች አጠቃሎ የያዘውና የሰው ልጅ አምልኮቱን በአግባቡ ለመፈጸም የሚያስፈልጉትን መመሪያዎችና በዱንያም በአኼራም ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ብሎም መልካም ሕይወት እንዲኖር የሚረዱትን መመሪያዎች ሁሉ አጠቃሎ የያዘው ታላቁ ቁርኣን ነው፡፡ ይህ ታላቅ ቁርኣን ታዲያ በትኩረትና በማስተንተን ሊነበብ ይገባዋል፡፡

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: