ቁርኣንን ማን ፃፈው?

2.00 $

ምዕራባዉያን ቁርኣንን በጥልቀት ሳያጠኑ እና ሳይገነዘቡት በሩቁ ሊያጣጥሉት ብዙ ሞክረዋል፡፡ ሊያጠለሹትም ብዙ ጽፈዋል፡፡ የሰው ድርሰት በተለይ የታላቁ የነቢያችን ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) የእጅ ዉጤት እንደሆነ አድርገው ሊያስተባብሉትም ደክመዋል፡፡  ይህ አነስተኛ መጽሐፍ “ቁርኣንን ማን ፃፈው?” በሚለው ጉዳይ ዙሪያ እነኚህ ወገኖች ለሚያነሱት ተደጋጋሚ ጥያቄ በማስረጃ አስደግፎ አጥጋቢ ምላሽ ይሠጣል፡፡ ብዥታዎችንም ያጠራል፡፡
ዝግጅት ፡ ሜምፊስ ደዕዋ
ትርጉም ፡ አሕመድ ሑሴን (አቡ ቢላል)
የገጽ ብዛት ፡ 39
የታተመበት ዓመት ፡ ሚያዚያ 2001
ከመጽሐፉ ፡ “ቁርኣንን ማን ፃፈው?” የሚለዉን ጥያቄ አስመልክቶ የሚነሱ አስተያየቶችን በሦስት ልንከፍላቸው እንችላለን፡፡ አንደኛው ፡ ቁርኣንን ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ዉ.) ፅፈዉታል የሚለው ነው፡፡ ሁለተኛው ፡ ቁርኣንን አንድ የሆነ ሰው አንደፃፈዉና ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዳስተማራቸው የሚነገር ሲሆን ሦስተኛው ደግሞ ፡ ቁርኣን የአንድዬ ፈጣሪ የአላህ (ሱ.ወ.) ቃል እንደሆነና የሰው ድርሰት እንዳልሆነው የሚነሳው ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ እነኚህን የተነሱ ሀሳቦች አጠር ባለ መልኩ ለመዳሰስ እንሞክራል፡፡ ሀሳቦቹን ከዳሰስን በኋላ መደምደምያ ነጥቦቹንም እናሰፍራለን፡፡ ….

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: