ቁርኣንን ለማንበብ

2.00 $

ቁርኣን የሙስሊሞች መመርያ እንደሆነ እሙን ነው፡፡ የወረደዉም በዐረብኛ ቋንቋ ነው፡፡ ይህ መመርያ ምን መልዕክት እንደሚያስተላልፍ ለማንበብም ሆነ ለማወቅ ዐረብኛን ማወቅ እና ፊደላቱን መለየት ያስፈልጋል፡፡ የአነባብ ስልቱን ለማወቅ የዐረብኛን ፊደላት ማወቅ ግድ ይላል፡፡ የዐረብኛ ፊደላት ከከንፈር፣ ከአፍ እና ከጎሮሮ የሚወጡ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ፊደላት ተመሳሳይ ሆነው የመውጫ ቦታቸው ብቻ የሚለያይበት ሁኔታ አለ፡፡ ተመሳሳይ የሆኑትን ከነቅላፄያቸዉና መውጫ ቦታቸው መረዳት ይገባል፡፡ ይህ መጽሐፍ የዐረብኛ ቋንቋ ፊደላትን፣ የፊደላቱን አነባብ፣ ቅርጽና አገባባቸዉን በዐረብኛና በአማርኛ የሚተነትን ነው፡፡ በተጨማሪም የማጥበቂያና የማርዘሚያ፣ በግልጽ የማውጣት፣ የመጨፍለቅየመደበቅና የመገልበጥ ስልቶችን በዝርዝር ያስረዳል፡፡
አዘጋጅ ፡ ዐብዱልመናን ከበደ (አቡ ያሲር አልጊላኒ)
የገጽ ብዛት ፡ 60
የታተመበት ዓመት ፡ 1995
ከመጽሐፉ ፡ ቁርኣንን መማር ግዴታ ነው፡፡ ቁርኣንን ማንበብ መቻል የኢስላማዊ ዕውቀቶች መፈለጊያ መሠረት መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ ቁርኣን የሕይወታችን መመርያ የፈጣሪያችን አላህ መልዕክት ነዉና፡፡ ይህ መማርያ የተለያየ መጽሐፍትን በማገናዘብና የመምህራንን ምክር መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ ነው፡፡
ከመጽሐፉ ፡

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: