ሸይኽ ኢብኑ ተይሚያ

4.00 $

እስልምና በየጊዜው በርካታ ተግዳሮቶችን አልፏል፡፡ በየዘመኑም ትንታግ በሆኑ ሊቃዉንቶቹ ታግዞ በርካታ መሰናክሎችን ተሻግሯል፡፡ በኢስላም ታሪክ ዉስጥ ትልቅ የዕውቀት እና የተሃድሶ አሻራ ትተው ካለፉ ሙስሊም ልሂቃን መካከል ሸይኽ ኢብኑ ተይሚያ አንዱ ናቸው፡፡ የርሣቸው አመለካከት መንገድና አስተምህሮ ዛሬም ድረስ ትልቅ ተጽእኖ አለው፡፡ ኢብኑ ተይሚያን ጠበቅ ባለ አቋማቸው ብዙዎች ቢቃወሟቸውም ስለ ታላቅ ምሁርነታቸው ግን ጠላቶቻቸው ጭምር ይመሰክሩላቸዋል፡፡ የኢማሙን የዕውቀት እና የትግል ሕይወት ጊዜ ወስደን ብንዳስስ በርግጥም በርሣቸው ላይ ይቀርቡ የነበረ ክሶች የተንሻፈፉ፣ የተጋነኑ አሊያም መሠረተ ቢስ መሆናቸውን እንረዳለን፡፡ ወጣቱ አሰላሳይ ሙሐመድ ዐሊ (ቡርሃን) የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ የኢብኑ ተይሚያን ማንነትና ተጋድለዎን ይዳስሳል፡፡
አዘጋጅ ፡ ሙሐመድ ዐሊ
የገጽ ብዛት ፡ 168
የታተመበት ዓመት ፡ 2009
ከመጽሐፉ ፡
በአንድ ዕለት የብዙሃኑ ስጋት እውን ሆነ፤ ወጣቱ የጥበብ አርበኛ በመንግስት ጀሌዎች ተያዘ፡፡ ወደ እስርም ተጣለ፡፡ መርዶውም ከእናቱ ጆሮ ደረሰ፡፡ በከፍተኛ ድንጋጤና ሀዘን ውስጥም ገባች፡፡ በምንም መልኩ ልጇ ነጻ እንደማይወጣ አምናለች፡፡ ይገድሉታል ወይም ክፉኛ ያሰቃዩታል ስትልም ደመደመች፡፡
የታሰረው ወጣት ኢብን ተይሚያህ ይባላል፡፡ ይዞ የመጣው ሀሳብ ለዘመኑ እንግዳ ስለነበር ከብዙሃኑ የአካባቢው ነዋሪ ጋር መስማማት አልቻለም፡፡ ጉዳዩ ለፖለቲካ አለቆችም ስላልተመቸ ነው ለእስር የተዳረገው፡፡ መታሰሩን ተከትሎ የእናቱን ጭንቀት ያስተዋለው ወጣት ቀጣዩን ደብዳቤ ፅፎ ከግብፅ እስር ቤት ወደ ደማስቆ ላከ፡፡ የደብዳቤው መልክት እንዲህ ይላል፡-

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 163 g