ሶላትን አደራ

2.00 $

ትልቅ ቁምነገርና መልዕክት ይዛለች፤ ስለ ሶላት ምንነት፣ ዓላማና ሚስጢር ትዳስሳለች፣ ጥቅሟን እና ትሩፋቷን ታስቃኘናለች፣ አለመስገድ ከባድ ወንጀል እንደሆነ ታስታውሰናለች፣ ሶላት የማይሰግድ ሰው ስለሚጠብቀው ቅጣት ታወሳለች፣ ሙስሊም ሆኖ ያለ ሶላት ሰውነት ያለ አንገት ማለት ነው ትላለች፣ ሶላት ባትኖር ኖሮ ክፉኛ እንደምንጎዳ ታሳያለች፣  ሶላት ጀነት ነውና ኑ ወደ ጀነት ግቡ! ብላ ትጣራለች!!! መጽሐፏ በተለይ በሶላት ጉዳይ ችላ ለሚሉ አሊያም ለማይሰግዱ፣ ወይም ደግሞ ዓላማዋንና በአግባቡ ላልተረዱትና ለሌሎችም በስጦታ መልክት ብትበረከት እጅግ ጠቃሚ ናትና የመልዕክቷ ተቋዳሽና አድራሽ  ይሆኑ ዘንድ በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡
አዘጋጅ ፡ ሙሐመድ ሰዒድ
የገጽ ብዛት ፡ 64
የታተመበት ዓመት ፡ ጥር 2010
ከመጽሐፉ ፡
የሰው ልጅ በምድር ላይ የመፈጠሩ ዋና ዓላማ አላህን (ሱ.ወ.) ለማምለክ እንደሆነ እርግጥ ነው፡፡ አምልኮ ሲባልም ዓይነቱ ብዙ ነው፡፡ አላህን (ሱ.ወ.) ከምናልክባቸው መንገዶች አንዱ ግዴታ የተደረጉብንን በቀን ዉስጥ አምስት ሶላቶችን በመወጣት ነው፡፡ በሶላት ለአላህ ባርነታችንን እንገልፃለን፡፡ ሰዎች ቃለ ተውሒድን ተቀብለው ወደ እስልምና የገቡ እንደሆነ ጥሪ የሚደረግላቸው ጠሃራ አድርገው ሶላት መስገድ እንዲጀምሩ ነው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ታላቁን ሶሐባ ሙዓዝ ኢብኑ ጀበልን ወደ የመን ሲልኩት እንዲህ ነበር ያሉት …..
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

 

Category: