ስለ ኢስላም

4.00 $

ከዚህ ቀደም ስለ እስልምና ሃይማኖት ምንነት በተለያዩ ቋንቋዎች በርካታ መጽሐፎች ተጽፈዋል። ከፊሎቹ በሰፊውና በጥልቀት የተዘጋጁ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ አጠር ያሉ ናቸው። ይህ መጽሐፍ በሁለቱ መካከል ሆኖ በተለይ ወደ እስልምና አዲስ ለሚገቡ አማኞች ታስቦ የተዘጋጀ ነው። የመጽሐፉ ዋና ዓላማም አዳዲስ ወደ እስልምና የሚመጡ ሰዎች መሠረታዊ የሆኑ የእስልምና አስተምህሮዎችን ማወቅና መተግበር ይችሉ ዘንድ ምልከታ ይሰጣል፡፡
እስልምና ምንድነው? የብዙዎች ጥያቄ ነው። ስለ እስልምና ማወቅ የሚፈልጉ ወገኖችም ብዙ ናቸው። በርግጥ በአንድ ጀምበር ስለ እስልምና ሁሉን ነገር በዝርዝር ማወቅ አዳጋች ነው። ሆኖም ግን በጉዳዩ ላይ ያለውን ክፍተት በማሰብ የተወሰነ ብርሃን ለመርጨት ያህል ይህ መጽሐፍ ተዘጋጅቷል፡፡
መጽሐፉን ለማዘጋጀት ከቀደሙት መጽሐፍት በርካታ መረጃዎችን ተካተዋል።
አዘጋጅ ፡ ሙሐመድ ሰዒድ
የገጽ ብዛት ፡ 160
የታተመበት ዓመት ፡ 2010
ከመጽሐፉ ፡
እስልምና በአንድ አምላክ (አላህ) አምልኮ ላይ መሰረቱን ያደረገ እምነት ነው። እስልምና ቀደምት ሃይማኖቶችን ሁሉ የሻረ የምድራችን የመጨረሻው ሰማያዊ ሃይማኖት ነው። ይህ ሃይማኖት ዛሬ በዓለማችን ላይ ከ2 ቢሊዮን በላይ ተከታዮች አሉት። የሃይማኖቱ ተከታዮች በብዛት የሚገኙትም በዋናነት በኢስያ በተለይ በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በአፍሪካ ደግሞ በዋናነት በሰሜን እና በሰሜን ምሥራቅ አካባቢዎች ነው። እስልምና በዓለም ላይ በእጅጉ እየተስፋፉ ካሉ ሃይማኖቶች መካከል የቀዳሚውን ቦታ የያዘ ሃይማኖት መሆኑን ጥናቶች ይጠቁማሉ። ከአውሮፓ እስከ አውስትራሊያ፣ ከሰሜን አሜሪካ እስከ ላቲን አሜሪካ ዛሬ ላይ ይህ ሃይማኖት ያልደረሰበት የዓለም ክፍል የለም።
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 35 g