ሴቶች በረመዳን

3.00 $

በረመዷን ዉስጥ ሴቶች ከወንዶች የተለየ መልኩ ወሩን ያሳልፋሉ፡፡ በቤት ዉስጥ ጉዳዮች ስለሚያተኩሩ ከረመዷን ትሩፋት ቀጥተኛ በሆነ መልኩ ተጠቃሚ የሚሆኑት ጥቂቶች ናቸው፡፡ መጽሐፉ ሴት ልጅ ረመዷንን በምን መልኩ ማሳለፍ እንዳለባት፤ ለሙስሊሟ ሴት የተበረከቱ ጠቃሚ ምክሮችና ስለ ረመዳን አጠቃላይ ግንዛቤ የሚሰጡ መጣጥፎች የተካተቱበት፤ ሴቶች በረመዳን ወር ማድረግና ማወቅ ስለሚገባቸው ነገሮችን አካቷል፡፡ ለየት ባለ አቀራረብ የተዘጋጀ በርካታ ዋቢ መጽሐፍትን ደራሲዋ ያጣቀሰችበት ነው፡፡ በረመዳን የሴቶች ሥራ የማጀት፤ የወንዶች ደግሞ የመስጊድ ብቻ ተብሎ የተወሰነ ይመስል በርካታ እናቶቻችንና እህቶቻችን ከዒባዳ ተዘናግተው ራሳቸውን በጓዳ አግተው ወሩን ሳይጠቀሙበት ያልፋቸዋል፡፡

አዘጋጅ ፡ ሸይማእ ሙስጦፋ

የገጽ ብዛት ፡ 87
የታተመበት ዓመት ፡ ሐምሌ 2003

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 93 g