ሳይንሣዊ ተዓምራት በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ሐዲሥ ክፍል ሁለት

$3.00

አላህ (ሱ.ወ.) ነብያትን ወደ ሰዎች ሲልክ ተዓምራትን አስይዞ ነው የላካቸው፡፡ ተዓምራቶቹም ከተጨባጭ እና በተለምዶ ከምናውቃቸው ነገሮች የተለዩ ናቸው፡፡ የተላኩ የአላህ ነብያት በእውነት ከአላህ ዘንድ የተላኩ ስለመሆናቸው ለማረጋገጥ ተዓምራቶቹን በማሳየት ሕዝቦቻቸዉን ለማሳመን ይሞክራሉ፡፡ ይህ መጽሐፍ በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) የተነገሩ ሐዲሦችን መሰረት ባደረገ መልኩ  ሐዲሦቹ የያዟቸው ሳይንሳዊ ተዓምራቶች የተቃኙበት ነው፡፡ ፕሮፌሰር ዘግሉል አን-ነጃር የሚደንቅና ለየት ያለ የኢስላምን አስተውሎቶች ከዘመናዊው ሳይንስ ጋር አሰናስሎ የማየትና ይህንንም ለተደራሲው  ፍንትው አድርጐ የማሳየት ብቃት ያላቸው ምሁር ናቸው፡፡ በዚህ ሥራቸውም በነቢያዊ ሐዲሥ የተነገሩትን መልዕክቶች ከሳይንስ ጋር አቆራኝተው ይተነትኑልናል፡፡
መጽሐፎቹ በሁለት ክፍሎች የተዘጋጁ ሲሆን ክፍል አንድ በ96 ገፆች፤ ክፍል ሁለት ደግሞ በ87 ገፆች የተጠናቀረ ነው፡፡
አዘጋጅ ፡ ፕሮፌሰር ዘግሉል አን-ነጃር
ትርጉም ፡ አሕመድ ሑሴን (አቡ ቢላል)
የገጽ ብዛት ፡ 96 እና 87
የታተመበት ዓመት ፡ መጋቢት 2001
ከመጽሐፉ ፡ በመጽሐፉ ዉስጥ ከተዳሰሱት ጉዳዮች ጥቂቶቹን እነሆ-
1- የምድር ዉስጣዊ ክፍል አወቃቀር፣
2- በፍርዱ ቀን የሰማያት መጠቅለል፣
3- ከዋክብት የቅርቢቱን ሰማይ ፀጥታ ይጠብቃሉ፣
4- ፀሐይ በምዕራብ በኩል ትወጣለች፣
5- የጨረቃ ተገምሶ መውደቅ፣
6- በየዓመቱ ተመሳሳይ መጠን ያለው ዝናብ ይዘንባል፣
7- ተራሮች የተቸከሉት ምድር እንዳትናወጥ ነው፣
8- ስለ ሰው ልጅ አፈጣጠር እርከኖች፣
9- ጥቁር አዝመድ ለሁለም በሽታ መድኃኒትነት፣
10-  እንጉዳይ የታመመን ዐይን እንደሚያድን፣
11-  የወይራ ዛፍ የተባረከ ስለመሆኑ፣
12-  ፆም ለጤንነት የሚሠጠው ጠቀሜታ፣
ሌሎችም

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

 

Category: