ሲራ

4.00 $

በሰነድ የተደገፈ ከግነትና ከተረት ተረት ነፃ የሆነ ቁልጭ ያለ ታሪክ ያለው ታላቅ ሰውና ነቢይ ቢኖር ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ብቻ ናቸው፡፡ አንዳንድ ምዕራባዊ ሃያስያንም “በቀን ብርሃን የተወለደ ሰው ቢኖር ሙሐመድ ነው፡፡” ማለታቸው ይታወሳል፡፡ ይህ መጽሐፍ የታላቁ ነቢይ የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) የሕይወት ታሪክና ገድል የተዳሰሰበት ነው፡፡ መጽሐፉ ከቁርኣን፣ ከሱና በነብዩ ዘመን ከታቀኙ ቅኔዎችና ከታሪክ መዛግብት የተውጣጣ ነው፡፡ ሙስጦፋ ሲባዒ በታሪክ አፃፃፍ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ናቸው፡፡ ተርጓሚዉም ባማረ ሁኔታ አቅርቦታል፡፡
ዝግጅት ፡ ሙስጠፋ አስ-ሲባዒ
ትርጉም ፡ ዶ/ር ኢድሪስ ሙሐመድ
የገጽ ብዛት ፡ 176
የታተመበት ዓመት ፡ 1991
ከመጽሐፉ ፡ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) በተላኩ በ10ኛው ዓመት አጎታቸው አቡ ጧሊብ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ በሕይወት እያሉ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ተከላካይና ተቆርቋሪ ጠበቃ ነበሩ፡፡ በነበራቸው ክብርና ተፈሪነት ምክንያት ቁረይሾች ነቢዩ ላይ አደጋ ለመፍጠር አልደፈሩም ነበር፡፡ ከአቡ ጧሊብ ሞት በኋላ ግን …
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 174 g