ሰፊና የአማርኛ ትርጉም

3.00 $

ሰፊና በሙስሊሞች ቤት በብዛት ከተሠራጩ በመጠን አነስተኛ ከሆኑ የፍቅህ መጽሐፎች መካከል አንዱ ነው፡፡ የሻፊዒያን መዝሀብ መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡ ብዙ ወላጆች ትናንሽ ልጆቻቸዉን የሰፊናን መጽሐፍ በማስተማር ነው የሚጀምሩት፡፡ በኡስታዝ ተውፊቅ ባሕሩ ወደ አማርኛ የተመለሰ የፊቅሂ መጽሐፍ ሲሆን በተለይ ለቂርኣት ጀማሪዎች፣ ለመድረሳ ተማሪዎችና ለሌሎችም እጅግ ጠቃሚ የሆነ፤ ሰፋ ካለ ማብራሪያ ጋር የተዘጋጀ ነው፡፡ መጽሐፉ በተለምዶ ‹ሰፊነቱ-ን-ነጃ› በመባል ይታወቃል፤ “የመዳኛ ታንኳ” ማለት ነው፡፡

አዘጋጅ ፡ ሳሊም ኢብን ሰሚር አል-ሐድረሚ
ትርጉም ፡ ኡስታዝ ተውፊቅ ባህሩ
የገጽ ብዛት ፡ 175
የታተመበት ዓመት ፡ መስከረም 2007
ጥቂት ከመጽሐፉ ፡
ለአካለ መጠን የመድረስ ምልክቶች ሦስት ናቸው፡-
1ኛ፡- ወንድም ሆነ ሴት አስራ አምስት ዓመት መሙላቱ፤ 2ኛ፡- ለወንድም ሆነ ለሴት ከዘጠኝ ዓመት በኋላ የፍትወት ፈሳሽ (መውጣቱ)፤ 3ኛ፡- ለሴት ከዘጠኝ ዓመት በኋላ የወር አበባ (መታየቱ)፡፡
ኒይያህ ማለት፡- አንድን ነገር ከድርጊቱ ጋር አቆራኝቶ ማሰብ ማለት ነው (ልበ-ውሳኔ)፡፡ ቦታውም ልብ ነው፡፡ ኒይያን በንግግር መግለፅ ሱንና ነው፡፡ (በዉዱእ ጊዜ) የኒይያው ወቅት ከፊቱ የመጀመሪያው ክፍል በሚታጠብበት ወቅት ነው፡፡
ቅደም ተከተሉን መጠበቅ (ተርቲብ) ማለት አንድን የዉዱእ አካል ከሌላው አለማስቀደም ማለት ነው፡፡
አሳታሚ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 161 g