ሰው እና ሰይጣን

1.00 $

ለመኾኑ ሰይጣን ማን ነው! ከአእምሮአችን ውል የሚልና መልስ የማይገኝለት የዘወትር ጥያቄ፡፡ ሰይጣን ረቂቅ ፍጡር ነው፡፡ ስለዚህም እርሱ እንደሚያየን ሁሉ በዐይናችን በብረቱ እንመለከተው ዘንድ አይቻለንም፡፡ ሲሻው በውል ከማንለየው አድራሻ(ሥፍራ) ኾኖ ሥርአተ ሃሳባችንን እንዳሻው ይዘውረዋል፡፡ በል ሲለው ከየ እዝነልቦናችን በመጠጋት በረቂቅ ቃላቱ ክፋቱን ያንሾካሹካል፡፡ ይህንና ተያያዥ ጥያቄዎችን መጽሐፉ ይመልስልናል፡፡
አዘጋጅ ፡ ሙሐመድ ሙተወሊትዋሊ አሽ-ሸዕራዊይ
ትርጉም ፡ ዒማዱዲን ዙልፊቃር
የገጽ ብዛት ፡ 106
የታተመበት ዓመት ፡ ሐምሌ 2005
ከመጽሐፉ : የተረገመው ሰይጣን ለአደም እና ዘርማንዘሩ ጠላትነትን ያወጀ ጠላት እኩይ ነው፡፡ አጅሬው ሰይጣን ‘ለአደም (ዐ.ሰ) መስገድ አሻፈረኝ’ ብሎ ካመፀባት ቅፅበት ጀምሮ በአድራጎቱ የመፀፀትም ኾነ እውነታውን የመቀበል ፍላጎት አላሳየም፡፡ ‘ጌታዬ ሆይ! ቃልህ እውነት ናት፡፡ ትዕዛዝህም እንዲሁ፡፡ ማረኝ;’ አላለም፡፡ በትምክህቱ በመቆጨት ተነስቶ አልሰገደም፡፡ እንዲያውም በትዕቢት አበጠ፡፡ በግትር ኩነኔውም ፀና፡፡

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: