Weight | 148 g |
---|
ሰላሑዲን አል-አዩቢ
$3.00
በዚህ መጽሐፍ ምዕራፎች ውስጥ አንድ ዐረብ ያልነበረ ኩርዳዊ ግለሰብ፡- እንዴት አድርጐ በኢስላም ታሪክ ዉስጥ ትላልቅ ድሎችን ሊያሳካ እንደቻለ፣ ተበጣጥሶ የነበረውን ሙስሊም ዑማ እንዴት በተዋጣለት አመራሩ ሥር ወደ አንድነት እንዳመጣ፣ ሕዝቡ ኢስላማዊውን ሸሪዓ እንዲከተል እንዴት ለማሳመን እንደበቃ፣ የአላህን ቃል የበላይ ለማድረግ እንዴት በኢስላም ስም እንደታገለ እና ጠላቶቹን እንዴት በመልካም ባህሪዎች እና ሥነ-ምግባሮች እንደያዛቸው አንባቢያን ይርረዱባቸዋል፡፡ እንዲሁም ከሌሎች ተለይቶ ይታወቅባቸው የነበሩ ምርጥ ባህሪዎቹን እና ያሳካቸውን የተሐድሶ ተግባራት ያውቁባቸዋል፡፡ ባጭሩ ሰላሑዲን ማን እንደነበር በሚገባ ይመለከቱባቸዋል፡፡
አዘጋጅ ፡ ዐብደላህ ናሲሕ አል-ዑልዋን
ትርጉም ፡ ዐብዱልከሪም ታጁ
የገጽ ብዛት ፡
የታተመበት ዓመት ፡ የካቲት 2006
ከመጽሐፉ ፡
የመስቀል ዘመቻዎች ያለማቋረጥ ለሁለት ክፍለ ዘመናት በአውሮፓዊያኑ የተደረጉ ወታደራዊ ዘመቻዎች ነበሩ፡፡ የዘመቻው ዋና ዓላማም እየሩሳሌምን ከሙስሊሞች እጅ መንጠቅና እስልምና የተቀረውን ዓለም ለመሸፈን እያደረገ የነበረውን ግስጋሴ መግታት ነበር፡፡ ሌሎች ምክንያቶችም ነበሩ፡፡ … በመጨረሻም ሰላሑዲን በመስቀል ወራሪዎች ላይ ትልቅ ድል ተቀዳጀ፡፡ ይህ የመስቀል ወራሪዎችን አንገት ያስደፋ ድል የተገኘው ግን ባጋጣሚ አልነበረም፡፡ የሙስሊሙ ሠራዊት በጣም የተደራጀ፣ በጣም የሰለጠነ፣ እጅግ ሥርዓት ያለውና በመርህ የሚመራ ሠራዊት ስለነበር ነው ለድል የበቃው፡፡ የጦርነት ቦታዎችንና ትክክለኛ ጊዜያቶችን በመወሰን በኩልም ወታደራዊ ብቃት ነበራቸው፡፡ ለዚህም ነበር ጦርነቱ ለመስቀለኞቹ የማያዳግም ዱላ የሆነባቸው፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት