ሪያድ አስ-ሷሊሒን ቅጽ 1 ስስ ሽፋን

9.00 $

የሪያዱሷሊሒን መጽሐፍ በዓለማቀፍ ደረጃ እጅግ ተነባቢ ከሆኑየሐዲሥ መጽሐፎች አንዱ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ያልገባበት የሙስሊም ቤት አለ ብሎ ማሰብ ይከብዳል፡፡ መጽሐፉ በአምልኮት፣ በመልካ ሥራዎችና በማኅበራዊ ጉዳዮች ዙርያ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ በዚህም ሆነ በመጨረሻው ዓለም ለስኬት የሚያበቁ ነቢያዊ (ሰ.ዐ.ወ.) ሐዲሦች ከነማብራሪያቸው ተካተዉበታል፡፡ መጽሐፉ በሁለት ትላልቅ ቅፆች የተዘጋጀ ሲሆን ወደ 1900 አካባቢ ሐዲሦችን ይዟል፡፡ የመጀመርያው ቅጽ (ሐዲሥ ቁ- 1-810) ይዟል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ከ (ሐዲሥ ቁ 1-811- 1896) ተካተዉበታል፡፡ ሁለተኛው
በስስ እና ጠንካራ ሽፋን የተዘጋጀ
አዘጋጅ – ኢማም አን-ነወዊ
ትርጉም – ኡስታዝ ሐሰን ታጁ
የገጽ ብዛት ፡ ቅጾች አንድ – 471፤ ቅጽ ሁለት- 496 ገጾች
መጠን ፡17*24
የታተመበት ዓመት ፡ ሐምሌ 2002
አንድ ሐዲሥ ከመጽሐፉ – ከአቢ ዘር (ረ.ዐ.) እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለዋል ‹በያንዳንዳችሁ የሰውነት መገጣጠሚያዎቻችሁ ላይ ሶደቃ /ምጽዋት/ ያለበት ሆኖ ያነጋል፡፡ እያንዳንዷ ተስቢሕ /ሱብሓነላህ/ ማለት ሶደቃ ናት፡፡ እያንዳንዷ ተሕሚድ /አልሐምዱ ሊላህ/ ሶደቃ ናት፣ እያንዳንዷ ተህሊል /ላኢላሀ ኢለላህ/ ሶደቃ ናት፣ እያንዳንዷ ተክቢር /አላሁ አክበር/ ሶደቃ ናት፣ በመልካም ማዘዝ ሶደቃ ነው፣ ከመጥፎ መከልከል ሶደቃ ነው፣ ሁለት ረከዐህ የምትሰገደው የዱሓ ሶላት ግን ይህን ሁሉ መተካት ትችላለች፡፡› (ሙስሊም ዘግበውታል፡፡)
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: