ሪያዱ ሷሊሓት

7.00 $

በተለይ በእስልምና መባቻ አካባቢ ሙስሊሟ ሴት ለኢስላም ያበረከተችው ሁለገብ አስተዋጽኦ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። በኢስላም የመጀመሪያዋ ሰማእት /ሸሂድ/ ሱመያ (ረ.ዐ.) መሆኗ ይታወቃል። እናታችን ዓኢሻ (ረ.ዐ.) ዲናዊ ዕውቀታቸው ጥልቅ ከመሆኑም በላይ ከሁለት ሺህ በላይ ነቢያዊ ሐዲሦችን አስተላልፈውልናል። በርካታ የሶሓባና ከዚያም በኋላ የተከተሉ ሴቶች በዕውቀት፣ በእምነት፣ በማኅበራዊ እንቅስቃሴ እና በሌላም ሌላም የሕይወት ዘርፍ ጉልህ ሚና ነበራቸው። ሆኖም ግን ዛሬ ላይ ሁኔታዎችን ስናጤን የሙስሊሟ ሴት የምድር ላይ አስተዋጽኦዋ ከፍ ያለ ሆኖ አይታይም። ከዚህም ከዚያም የሚደረጉባት ጫናዎች የበዙ ሆነው እናገኛለን። ሚናዋን ለማሳነስ የሚደረገው ጥረት ሁሌም አለ። ይህም አንድም የእስልምናን አስተምህሮ ባለማወቅ አሊያም ትምህርቶቹን በመዘንጋት ሊሆን ይችላል። ስለሆነም ይህንን ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ መግለፁና ማስታወሱ ግድ ይላል። እሷም በእስልምና ውስጥ የበኩሏን ሚና ትወጣ ዘንድ ማበረታታቱ ተገቢ ነው። ይኸው ታስቦ ይህችን ትንሽ መጽሐፍ ማዘጋጀት አስፈለገ። በመጽሐፉ ውስጥ እህቶች ብሎም ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች ጠቃሚ ነገር እንደሚያገኙበት ተስፋ እናደርጋለን።
አዘጋጅ ፡ ሙሐመድ ሰዒድ
የገጽ ብዛት ፡
የታተመበት ዓመት ፡ 2008
ከመጽሐፉ ፡ ከአነስ (ረ.ዐ.) እንደተወራው የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ‹ሁለት ሴት ልጆችን ለአካለ-መጠን እስኪደርሱ ድረስ የተንከባከበ የቂያማ ዕለት እኔና እርሱ እንደዚህ ሆነን እንመጣለን። ጣቶቻቸውን አጠጋግተው (እያሳዩ)። (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

አሳታሚ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: