ሪዝቅ

2.00 $

ሪዝቅ ስንል ሲሳይ ማለታችን ነው፡፡ ሲሳይ ደግሞ በምድር ላይ ስንኖር አላህ የሚሠጠንና ለኑሯችን የሚያግዘን ማንኛዉም ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ ከዕለት ጉርስ እስከ ትዳር፡፡ የሰው ልጅ ወደዚህ ምድር ከመምጣቱ በፊት ሲሳዩ ሁሉ ተጽፏል፡፡ ምን እንደሚሠራ፣ ምን እንደሚበላ ተከትቧል፡፡ ማንኛዋም ነፍስ ሲሳዩዋን ሳትጨርስ አትሞትም፡፡ ይህንን ምድር አትለቅም፡፡ ይህ መጽሐፍ ስለ ሪዝቅ እና መገኛ መንገዶቹ፤ ስለ ገንዘብ እና በረከቱ ይዳስሳል፡፡ ማንኛዉም ገንዘብ ነገ ምርመራ እኛ ስለሚጠበቅበት ሙስሊሞች ሐላል ሪዝቅ መፈለግና ለዚህም መጨነቅ እንዳለብን ያሳስባል፡፡
አዘጋጅ ፡ አብዱል መሊክ አል-ቃሲም እና ዶ/ር ዘይድ ቢን ሙሐመድ አሩማኒ
ትርጉም ፡ ጁነይድ ዐብዱልመናን
የገጽ ብዛት ፡ 126
የታተመበት ዓመት ፡ ግንቦት ፡ 2006
ከመጽሐፉ ፡ ሲሳይ ለማግኘት አብይ ምክንያት ሊሆኑ ከሚችሉ ነገሮች መካከል ከወንጀል መራቅ አንዱ ነው፡፡ ወንጀልን መዳፈር የዱንያንም የአኼራንም ኸይር ይዘጋል፡፡ አንድ የፍትህ ሊቅ (አላህን የሚፈራ ሰው ከችግሮቹ ሁሉ መውጫ በር ይከፍትለታል፤ ከማያስበውም በኩል ሲሳይን ይሰጠዋል ተብሎ ሲነገራቸው እንዲህ ነበር ያሉት፤ “አዎ በአላህ እምላለሁ! እኛ ተገቢውን መፍራት ሳንፈራውም መውጫ ያደርግልናል፤ ሲሳያችንንም ይሰጠናል፤ አላህን የሚፈራ ወንጀሉን ያብስለታል፤ ምንዳውንም ያተልቅለታል፤ ሲል የገባልንንም ቃል እንደምናገኝ ተስፋ እናደርጋለን፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 59 g