ሚዛናዊነት በሙስሊም ሕይወት ውስጥ

3.00 $

ዛሬ ላይ በርካታ ወገኖች ሚዛናዊ ነን ይላሉ፡፡ ይህ መጽሐፍ ስለ ሚዛናዊነት ምንነት፣ በነገሮች ዉስጥ ሁሉ ሚዛናዊ የመሆን አስፈላጊነት፣ ጠንካራ ፍላጎቶችንና የራስ ዝንባሌዎችን አመዛዝኖ ስለመያዝ፣ ሚዛናዊ ለመሆን ስለሚረዱ መንገዶች፣ ሚዘናዊነትን ለማረጋገጥ መሟላት ስለሚገባቸው ነጥቦችን ተያያዥ ጉዳዮች የተዳሰሱበት ነው፡፡
ዝግጅት ፡ ዶ/ር ሙሐመድ ሙሳ አሽ-ሸረፍ
ትርጉም ፡ ዐብዱልከሪም ታጁ
የገጽ ብዛት ፡ 104
የታተመበት ዓመት ፡ 2007
ጥቂት ከመጽሐፉ ፡
ውስጣዊ ስሜቶቹን መግራትና በሥርዓት መምራት የቻለ ሰው፣ ስኬታማ ይሆናል፡፡ ነፍሱ ልቅ ስሜቷን ተከትላ እንድትነጉድ እንዲሁ የለቀቃት ግን በእርግጥ ኪሳራ ላይ ይወድቃል፡፡ እንደዋለለም ይኖራል፡፡ ዛሬ፣ ኡማውን ወደ ቀድሞ የክብር ደረጃው የመመለሱ ኃላፊነት በእያንዳንዱ ሙስሊም ግለሰብ ላይ ተጥሏል፡፡ ይህን ኃላፊነቱን የሚወጣበት መንገድ ደግሞ፣ በመጀመሪያ ራሱን ማስተካከልና ቀጥሎ ለሌሎች ጥሪ ማድረግ ነው፡፡ ነፍሱን ገርቶ፣ ራሱን መርቶ፣ በሁሉም አቅጣጫ የተስተካከለና ያማረ ስብዕና መላበስ የሁሉም ሙስሊሞች ትልቅ ግብ ቢሆንም በቀላሉ የሚሳካ ግን አይደለም፡፡ በርካታ እንቅፋቶች አሉበት፡፡ በተለይ በዚህ ዘመን ትላልቅ እንቅፋቶች ተጋርጠውበታል፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: