ሙስሊሞች ለአለም ስልጣኔ ምን አበረከቱ?

2.00 $

ሙስሊሞች ዓለም ሥልጣኔ ያበረከቷቸዉን ነገር እንቁጠር ቢባል ባህርን በጭልፋ ነው የሚሆነው ፡፡ ግና ያሉትንና ለዘመናት ሊወሱ የሚችሉትን አበርክቶዎች በማህበራዊ ኑሮ፣ በአመለካከት፣ በአምልኮት፣ በሳይንስና በሌላም ረገድ የሙስሊሞች በዚህች ተማሪዎች በተረጎሟት ትንሽ መጽሐፍ  ለመቃኘት ተሞክሯል፡፡ መጽሐፏ አነስተኛ ብትሆንም ትልቅ ቁምነገርና ትምህርት የምታስጨብጥ ናት፡፡
ዝግጅት ፡ ዶ/ር ጀማል በደዊ
ትርጉም ፡ አወሊያ 98 ጀመዓ
የገጽ ብዛት ፡ 56
የታተመበት ዓመት ፡ መስከረም 2002
ከመጽሐፉ ፡  ታዋቂው የታሪክ ምሁር ሮብ ብሪፎልት በመጽሐፉ ዘመናዊው የአውሮፓ ሥልጣኔ አሁን ያለበት ደረጃ የደረሰው በዐረቦች ጥረት ነው ይላል፡፡ በዚህም የተነሳ የእስልምና የባህል ተጽዕኖ ያላረፈበት አንድም የአውሮፓ ዕድገት የለም ማለት ይቻላል፡፡ ሳይንስ በአውሮፓ የመከሠቱ ምክንያት አዲስ የመንፈስ ጥንካሬ፣ የጥናትና ምርምር ዘዴ ቅየሳ፣ በተግባር የታገዘ ጥናት፣ እና የመሞከር ሥራን ከሂሳብ ጋር አቆራኝተው በመጠቀማቸው ነው፡፡ … የዚህ ሁሉ ምንጩ ሙስሊሞች ናቸው ….
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: