ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ

4.00 $

ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች በሙስሊም ኅብረተሰብ ውስጥ ያላቸውን መብት ቁርኣንና ሐዲስ ያስተምረናል፡፡ ኢሥላም የመቻቻል ፖሊሲው ምን ያህል እንደሆነ ለማሳወቅ ዩሱፍ አልቀርዷዊ ይህን መጽሐፍ አዘጋጅተዋል፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ የተለያዩ ኅብረተሰቦች፣ እምነቶች፣ ሃይማኖቶችና ባሕሎች ለሚገኙባቸው አገሮች ተቻችሎ ለመኖር እና ሙስሊም ያልሆነው የኅብረተሰብ ክፍል ስለ ኢስላም ያለውን ግንዛቤ ለማዳበር ይረዳል ያለው ሐሰን ታጁ መጽሐፉን ተርጉሞታል፡፡
አዘጋጅ ፡ ኢማም  ፕ/ር  ዩሱፍ አልቀርዷዊ
ትርጉም ፡ አምባሳደር ኡስታዝ ሐሰን ታጁ
የገጽ ብዛት፡ 108
የታተመበት ዓመት ፡ ነሐሴ 2001
ከመጽሐፉ ፡ አንዳንዶቹ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖችን በተመለከተ ኢስላም የተከተለዉንና ጥንትም ሆነ ዛሬ በሰው ልጅ ታሪክ ዉስጥ አቻ የማይገኝለትን የመቻቻል ፖሊሲ ጥላሸት ለቂቡ ሞከሩ፡፡ ታሪክን አዛብተው፣ ያልተናገረዉን አጣመው አቀረቡ፣ የቁርኣንና የሐዲሥ ድንጋጌዎችን ትርጉም ለማዛባት ሞከሩ፡፡ ይህም ስለሆነ ከሙስሊሞችም ሆነ ሙስሊም ካልሆኑ ወገኖችም እውነትን ለሚፈልጉ ሁሉ ይህ መጽሐፍ የያዘው ጥናት ብዙ ነገሮችን ግልጽ ያደርግላቸዋል፡፡ …

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 107 g