ሙሐመድ የታላቆች ታላቅ

2.00 $

መጽሐፉ የነቢዩ ሙሐመድን ታላቅነት በማስረጃ በማስደገፍ ለማሳየት የሚሞክር ነው፡፡ ፀሐፊው ዓለማቀፉ ዳዒ ሸይኽ አሕመድ ዲዳት ሲሆኑ የተለያዩ የዓለማችን ታዋቂ ሰዎችን በማነፃፀር የነቢዩን ታላቅነት ያስረግጣሉ፡፡ የመጽሐፉ ይዘትም የዓለማችን ተጽእኖ ፈጣሪዎች እነማናቸው ይላሉ፡፡ ሚካኤል ሃርት ከዓለማችን የምንጊዜም መቶ ተጽእኖ ፈጣሪዎች መካከል ሙሐመድን ለምን መጀመርያ አስቀመጡ? ከፍተኛ ሥርጭትና መስፋፋት ያሳየው ሃይማኖት የትኛው ነው? ኢስላም በምንድነው የተስፋፋው? ኢስላም እንደሌሎች እነቶች ለምን አልከሰመም በማለትም ጥያቄዎችን እያሱ ምላሽ ይሠጣሉ፡፡ ስለ ኢስላም ድል አድራነት፣ ስለ ታላላቅ ሰዎች ምስክርነት፣ ስለ ሙሐመድ ጥረትና ዉጤትም ይተነትናሉ፡፡
ዝግጅት ፡ ሸይኽ አሕመድ ዲዳት
ትርጉም ፡ ዐሊ ሙሐመድ
የገጽ ብዛት ፡ 55
የታተመበት ዓመት ፡ ጥር 1987
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: