መስሩርና መቅሩር

3.00 $

ሁሉም ሞልቶ የተረፈው መስሩርና የሚልስ የሚቀምሰው ያጣው መቅሩር በአንድ ወቅት በገሐዱ ዓለም ይኖሩ ነበር፡፡ እነዚህና ሌሎች አስተኔ ገጸ ባህሪያት የተፈጠሩት በደራሲው አእምሮ ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች በዳይና ተበዳይ ሆነው የፍርድ ቀን (የውመል ቂያማ) ይገናኛሉ፡፡ ከአላህ ጋር ሂሳብ ተሳስበው መስሩር ወደ ጀሃነም መቅሩር ወደ ጀነት ይሄዳሉ… ታሪኩ እጅግ ጣፋጭና አጓጊ ነው፡፡ በጥሩ አማርኛ ውብ ተደርጐ ተተርጉሟል፡፡
አዘጋጅ ፡ አሕመድ በህጀት
ትርጉም ፡ አሕመድ ሁሴን (አቡ ቢላል)
የገጽ ብዛት ፡ 136
የታተመበት ዓመት ፡ ጥቅምት 2001
ከመጽሐፉ ፡ መቅሩር በቤቱ ወለል ላይ የበግ አጎዛ ለብሶ ከተኛበት ቦታ ፈንጠር ብሎ በመነሳት ሁኔታዉን ለመቆጣጠር ሞከረ፤ በዚህ ጊዜ ብርዱ አጥንቱ ድረስ ገብቶ ያንዘፈዝፈው ጀመር፤ ያም ቢሆን የእንጨት በሩን ለመዝጋት በመቻኮል የድንጋይ ማስደገፊያዉን እንደነበረ ከመለሰ በኋላ በላዩ ላይ እግሩን አሳርፎ ሁኔታዉን ይከታተል ጀመር፡፡ ንፋሱ ዳግመኛ በሩን እንደማይከፍትበት በማመኑ በብርድና በፍርሃት እንደታጀበ ወደ መኝታው አመራ … ….
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: