ሒክማ

2.00 $

ይህ መጽፍ የታላላቅ ዑለሞች ምርጥ ሥራዎችና ንግግሮች ስብስብ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ተነስተው የነበሩት አራቱ ታዋቂ ምሁራን ኢብን ሲና፣ አል ፈራቢ፣ አልገዛሊና አልኪንዲ በእውቀት፣ በሐዘንና መጽናናት የሞት ፍርሃትን በማስወገድ፣ የምቀኝነት ምክንያቶቹና መድኃኒቱ እንዲሁም ሌሎች የሰው ልጅ ችግሮች ላይ በማተኮር ያስተላለፉት ትምሕርት ነው በዚህ መጽሐፍ እጥር ምጥን ተደርጐ የቀረበው፡፡
ዝግጅት ፡ ዶ/ር ሙሐመድ አቡ ለይላ
ትርጉም ፡ አቢይ ጣሰው
የገጽ ብዛት ፡ 64
የታተመበት ዓመት ፡ ሚያዚያ 2001
ከመጽሐፉ ፡
ኢብኑል ሙባረክ “ዕውቀትን የማይፈልግ ሰው ግርም ይለኛል፤ እንዴት የተከበረ ሰው ሊሆን ይችላል!” ብለው ይጠይቃሉ፡፡ ሌላ አዋቂ ሰው ደግሞ ይህንን ይላሉ “ ለሁለት ሰዎች እንደማዝነው ለማንም አላዝንም፤ አንደኞቹ ዕውቀትን እየፈለጉ ዕውቀትን የማይረዱት ሲሆኑ ሁለተኞቹ ደግሞ የዕውቀትን ጥቅም ተረድተዉት የማይፈልጉት ናቸው፡፡”

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: